Voice of Truth and Life

Follow Voice of Truth and Life
Share on
Copy link to clipboard

Being a light in this world.

Donatist


    • Jan 29, 2022 LATEST EPISODE
    • daily NEW EPISODES
    • 34m AVG DURATION
    • 1,423 EPISODES
    • 14 SEASONS


    Search for episodes from Voice of Truth and Life with a specific topic:

    Latest episodes from Voice of Truth and Life

    በእምነት ማደግ ካለፈው የቀጠለ

    Play Episode Listen Later Jan 29, 2022 50:43


    አንዳንዱ የጸሎት መልስ መፍትሄ የሚመጣው ሳይታክቱ የእግዚአብሔርን ፊት በመፈለግ በጾም ጸንቶና ተግቶ በጌታ ፊት በመሆን በትግስት በእምነት እስከመጨረሻው ጌታን በመጠባበቅ የሚገኝ ድል ጉብኝት አለ

    እግዚአብሔር ይመራል

    Play Episode Listen Later Jan 5, 2022 49:41


    እግዚአብሔር የታደገን ሊመራን ቢሆንም፣ እኛ አማኞች ደግሞ በእርሱ ዓላማና ሐሳብ የተያዝንና እርሱን ለመከተል ፈቃደኛ መሆን አለብን፣ እግዚአብሔር ያለን ሰዎች ሆነን ግን ብዙ ጊዜ በራሳችን መንገድ እንሄዳለን በራሳችን ደግሞ ሁሉን ለማድረግ እንሞክራለን ሆኖም በአንድ ቦታ መዞር መጥመልመልና ድካምን ነው የምናተርፈው፣ ተስፋ የሚጣልበት እውነተኛው አምላክ እግዚአብሔር ሲመራን ግን እርሱ መንገድ በሌለበት መንገድ በጨለማ ውስጥ ደግሞ ብርሀን ይሆንልናል፣

    ወንጌልና መንግስተ ሰማያት

    Play Episode Listen Later Jan 5, 2022 23:57


    መልአክና ሰው የተፈጠረው ለአምልኮ ስለሆነ ወንጌልም ወደ ሕይወት ካመጣን በኃላ ወደ አምልኮ ነው የሚያደርሰን፣ በትክክለኛ አምልኮ ከአምላካችን ጋር ስንገናኝ የእግዚአብሔርን ትልቅነት እያየንና እግዚአብሔር በስራው ጻድቅ መሆኑን እየተረዳን በምናልፍበት ሁሉ እርሱን ማመስገን እንጀምራለን፣ መርገማችንን ሽሮ የመንግስቱ ወራሾች ያደረገን አምላካችን እዚህ ምድር ላይ ያስቀመጠን ለመንግስቱ ስራ መሆኑ ሲገባን ዛሬ የምለምናቸው ነገሮች ያንሱብንና በምስጋና እንሞላለን፣ በምስጋና ደግሞ ብዙ ቀንበራችን ይሰበራል ብዙ ድልንም እንቀዳጃለን፣

    ወደ ኢየሩሳሌም በምሕረት ተመልሻለሁ፤ ቤቴ ይሠራባታል

    Play Episode Listen Later Dec 29, 2021 43:25


    እግዚአብሔርን በታሪክ ውስጥ ስናየው እምነታችን ይጨምራል፣ መንፈሳዊ ሰው የሚኖረው በእምነቱ ስለሆነ እምነታችን ሲያድግ አንዳንዴ እግዚአብሔር እየተናገረ ያለው ባዶ በሆነ ነገር ላይና ለሰው በማይመስል ነገር ላይ የእግዚአብሔርን ሐሳብ ለማስተናገድ አንቸገርም፣ የእግዚአብሔርን ሐሳብ ለመበጥበጥ በሚመጣው ማንኛውም ነገር ባለመታወክ ፍቅሩንና ምህረቱን እያሰብን እግዚአብሔር የማያሳፍር አምላክ መሆኑንም በመረዳት፣ የሚታየውን የሚሰማውንና የምናስበውን ሳይሆን ጌታን ማየትና መስማት እንጀምራለን

    ያደገ ሰው ወደ ውስጥ የሚያስገባውን እና ከውስጡ የሚያውጣውን በቃሉ እና በመንፍስ ቅዱስ ይመዝናል 1ኛ ቆሮ 2:13 2ኛ ነገ 13 ሐዋ 17:11-28

    Play Episode Listen Later Dec 28, 2021 13:38


    ያደገ ሰው ወደ ውስጥ የሚያስገባውን እና ከውስጡ የሚያውጣውን በቃሉ እና በመንፍስ ቅዱስ ይመዝናል 1ኛ ቆሮ 2:13 2ኛ ነገ 13 ሐዋ 17:11-28

    በመንፍሳዊ ህይወታችን ሰናድግ ፈረሃት አይገዛንም ዕብ 2:14-15 1ዮሐ 4:18 ኢሳ 8:13 መሳ 6:10 ራዕ 21:8

    Play Episode Listen Later Dec 27, 2021 10:30


    በመንፍሳዊ ህይወታችን ሰናድግ ፈረሃት አይገዛንም ዕብ 2:14-15 1ዮሐ 4:18 ኢሳ 8:13 መሳ 6:10 ራዕ 21:8

    ዳግም መወለድና በንስሐ ወደ መንግስተ ስማያት መግባት

    Play Episode Listen Later Dec 27, 2021 25:39


    በንስሐ ወደ እግዚአብሔር እንደርሳለን፣ ጌታን እንደግል አዳኛችን አድርገን ስንቀበልና በሐጢያታችን ስንናዘዝ ጌታ ይቅር ይለንና ልጆቹ ያደርገናል፣ ዳግመኛ በእውነት ቃል ከማይጠፋው ዘር እንወለዳለን፣ ጌታን ካወቅን በኋላ ንስሐ ያልገባንበት ሐጢያት ካለ የእግዚአብሔር ለሆነው ነገር ጠንካሮች እንዳንሆንና በጉስቁልና እንድንኖር ያደርገናል፣ እግዚአብሔር ከሐጢያት ጋር ሕብረት ስለሌለው ከጌታ ጋር ህብረት እንዳይኖረንም ያደርጋል፣ ስለዚህ እራሳችንን ሁልጊዜ አየመረመርን በንስሐ የእግዚአብሔርን ፊት ልንፈልግ ይገባናል፣

    ዘካርያስ 3፡1-10 ክፍል ሁለት

    Play Episode Listen Later Dec 26, 2021 15:26


    ሰይጣን ደካማ ጎናችንን ያውቃል ነገር ግን ከዛ ውስጥ ጠንካራ ነገር ይወጣል። ይህ ጠንካራ ጎን የሚወጣው በሞትንበት ነው።

    በህይወቱ ያደገ ሰው የሰማውን ቃል የመጠበቅ ብቃት አለው በአንጻሩ ያላደገው ሰምቶ የመጠበቅ ብቃት የለወም ሕዝ 3:10 ሉቃ 8:13-15 2ኛ ጢሞ1:14 ራዕ 3:3 ኢዮ 20

    Play Episode Listen Later Dec 26, 2021 12:54


    በህይወቱ ያደገ ሰው የሰማውን ቃል የመጠበቅ ብቃት አለው በአንጻሩ ያላደገው ሰምቶ የመጠበቅ ብቃት የለወም ሕዝ 3:10 ሉቃ 8:13-15 2ኛ ጢሞ1:14 ራዕ 3:3 ኢዮ 20

    ዘካርያስ 3፡1-10 ክፍል አንድ

    Play Episode Listen Later Dec 25, 2021 55:18


    ጠላት ይከሳል ነገር ግን የሚሰምርለት ከውስጥ ከአካል ተባባሪ ካገኘ ብቻ ነው። ምክንያቱም ጌታ የቅዱሳን ክስ ስለማይሰማ። ይህም ፀጋን ብቻ እንድንመለከት ነው።

    ሰው እግዚያብሔርን ተስፍ ካደረገበት በላይ የህይወት አቅም የለውም ሮሜ 8፡24 ሮሜ 8:12 ዘፍ 13:10

    Play Episode Listen Later Dec 25, 2021 10:53


    ሰው እግዚያብሔርን ተስፍ ካደረገበት በላይ የህይወት አቅም የለውም ሮሜ 8፡24 ሮሜ 8:12 ዘፍ 13:10

    በፍቅር ማደግ

    Play Episode Listen Later Dec 24, 2021 46:13


    ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፣ ክርስቶስን የሚያውቅና የእርሱ ተከታይ የሆነ እማኝ ዋነኛው የባህሪው መገለጫ ፍቅር ሊሆን ይገባል፣ ጌታ እየሱስ እንኳን አንድ ሕግ አዋቂ ሊፈትነው ከሕግ የትኛይቱ ትእዛዝ ታላቅ እንደሆነች ሲጠይቀው የመለሰው መልስ፣ ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍሥህም በፍጹም አሳብህም ውደድ ታላቂቱና ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት ሁለተኛይቱም ይህችን ትመስላለች፥ እርስዋም ባልንጀራህን እንደ ነፍሥህ ውደድ የምትለው ናት ብሎ ነው፣ እንግዲህ በዚህ ፍቅር ለማደግ የመጀመሪያው ይቅር ማለት ሲሆን በመቀጠል ፍቅርን መከታተልና ከቅዱሳን ጋር ጤነኛ ህብረትን በመፍጠር ልንገለጽ ይገባናል፣ ክርስቶስ በምን ያህል ፍቅር እንደወደደን ሲገባን ሌሎችን ለመውደድ አንቸገርም፣

    እየሱስን በመመሰል ለመቀጠል

    Play Episode Listen Later Dec 24, 2021 39:00


    የእግዚአብሔር የሆነው ሁሉ መንፈሳዊ ነው፣ አኛ አማኞች ቃሉን ሆነን የምንገኘው በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ነው፣ ያለመንፈስ ቅዱስ የክርስቶስን ሙላት የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለስዎች ማድረስ አንችልም፣ ይህንን መንፈስ ቅዱስ ደግሞ ካልታዘዝን፣ ህሊናችን ንጹህ ካልሆነና ካልተጠማን መሞላት አንችልም፣ ጌታችን እየሱስ እራሱ ከመታዘዝ ጋር አያይዞታል፣ ትዕዛዛቱን ሁሉ ጥለን መንፈሱን መፈለግ አንችልም፣ ትዕዛዛቱን መጣል ማለት እታድርጉ የተባልነውን ማድረግና አድርጉ የተባልነውን ደግሞ አለማድረግ ነው፣

    ሰው እግዚያብሔርን ተስፍ ካደረገበት በላይ የህይወት አቅም የለውም ሮሜ 8፡24 ሮሜ 8:12 ዘፍ 13:10

    Play Episode Listen Later Dec 24, 2021 10:49


    ሰው እግዚያብሔርን ተስፍ ካደረገበት በላይ የህይወት አቅም የለውም ሮሜ 8፡24 ሮሜ 8:12 ዘፍ 13:10

    እግዚአብሔር ለመልካም ቀን ቀጥሮአል

    Play Episode Listen Later Dec 23, 2021 33:42


    እግዚአብሔር መልካም ስለሆነ ለህዝቡ ለመልካም ቀን ይቀጥራል። እኛ ግን በመታመን መጠበቅ አለብን። እግዚአብሔር ካለን ይልቅ ሁኔታን አይተን መናወጥ የላብንም። እስራኤል እግዚአብሔርን ከመስማት ይልቅ ጠላት የሚላቸውን ይሰሙ ስለነበር በምድረብዳ ቀርተዋል። እኛም ከጥርጠና ፍርሀት ሀሳባችንን መጋረድ እለብን። በዚህ ክፍል ውስጥ ይህንን በስፍት እንማራለን።

    ያደገ ሰው በጽጋ ይኖራል ሮሜ 7 ሮሜ 6:14 ሮሜ 6:11 ራዕ 12:10

    Play Episode Listen Later Dec 23, 2021 13:10


    ያደገ ሰው በጽጋ ይኖራል ሮሜ 7 ሮሜ 6:14 ሮሜ 6:11 ራዕ 12:10

    ለሰዎች መሆን ክርስቶስን መምሰል ሲሆን ዋጋ ያስከፍላል ዘኍ 16:45 ኢያ 3፡13 ዘኍ 16፡41

    Play Episode Listen Later Dec 22, 2021 11:07


    ለሰዎች መሆን ክርስቶስን መምሰል ሲሆን ዋጋ ያስከፍላል ዘኍ 16:45 ኢያ 3፡13 ዘኍ 16፡41

    ያደገ ሰው ጦር እቃው ምንድን ነው? ያላደገስ? 2ኛ ቆሮ 10 1ኛ ጵጥ 3

    Play Episode Listen Later Dec 21, 2021 9:46


    ያደገ ሰው ጦር እቃው ምንድን ነው? ያላደገስ? 2ኛ ቆሮ 10 1ኛ ጵጥ 3

    ባደገ ሰው ውስጥ ከሚታዮት ባህሪዎች ውስጥ ለሌሎችህ መስጠት ለራስ ከማድርግ በላይ ያስደስተዋል ዕብ 13:16 ሉቃ 6:38

    Play Episode Listen Later Dec 20, 2021 12:09


    ባደገ ሰው ውስጥ ከሚታዮት ባህሪዎች ውስጥ ለሌሎችህ መስጠት ለራስ ከማድርግ በላይ ያስደስተዋል ዕብ 13:16 ሉቃ 6:38

    ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች ተከታታይ ትምህርት

    Play Episode Listen Later Dec 20, 2021 26:07


    በእኛ መልካምን ስራ የጀመረው ልኡል እግዚአብሔር ስለ በጎ ፈቃዱ መፈለግንም ማድረግንም በህይወታችን የሚሰራው እስከ ኢየሱስ ክርስቶስ ቀን ድረስ እንዲፈጽመው የታመነ አምለክእ ነው

    1ኛ የዮሐንስ መልእክት ተከታታይ ትምህርት

    Play Episode Listen Later Dec 20, 2021 41:38


    የቤርያ ሰዎች ልበ ሰፊዎች ነበሩና ነገሩ እንደዚሁ ይሆንን ብለው ዕለት ዕለት መጻሕፍትን እንደመረመሩ እንደ እግዚአብሔር ቃል ሆኖ ሲያገኙት ደግሞ ቃሉን በሙሉ ፈቃድ እንደተቀበሉ አማኝ ከቃሉ ጋር የሚንሰማውን ሁልጊዜ ማመሳከር አለበት

    ክርስትያን የሚያድገው የፈርሰውን ያህል ነው ያደገ ሰው ይሰማል ምሳ 1:32-33 ሮሜ 10:10

    Play Episode Listen Later Dec 19, 2021 11:28


    ክርስትያን የሚያድገው የፈርሰውን ያህል ነው ያደገ ሰው ይሰማል ምሳ 1:32-33 ሮሜ 10:10

    ጥያቄ እና መልስ ክፍል 100

    Play Episode Listen Later Dec 19, 2021 46:58


    የዛሬ ጥያቂዎች 1. ነፃ የወጣ ሰው ነው ለእግዚአብሔር የሚሆነው ይህ ደግሞ እድገት ነው የሚለው ሀሳብ ይብራራልን። 2. ጌታን ስንቀበል በመንፈስ ቅዱስ ታትመናል ልጅ ለመሆን ግን ገና መንፈስ ቅዱስ አልተሞላንም የሚለው ሀሳብ አብራራልን። 3. የመንፈስ ቅዱስ ሙላት የሚሄደው ከመታዘዝ ጋር ነው የሚለውን ሀሳብ አብራራልን። 4. በመዳን ውስጥ ትልቅ ትንሽ የለም ወደ መንፈስ ቅዱስ ሙላት ስንመጣ ለእያንዳንዱ የተለያየ መለእክት አለው የሚለውን ሀሳብ አብራራልን። 5. በመንፈስ ቅዱስ የተሞላ የአሸናፊነት አቅም የሚኖረው ህይወታችን ነው የሚለውን ሀሳብ አብራራልን።

    ወዳጅነታችን እንደ ክርስቶስ ባህሪ የሆነ የማይለዋወጥ መሆኑ ማደጋችንን ያሳያል ምሳ 11:17

    Play Episode Listen Later Dec 18, 2021 13:16


    ወዳጅነታችን እንደ ክርስቶስ ባህሪ የሆነ የማይለዋወጥ መሆኑ ማደጋችንን ያሳያል ምሳ 11:17

    ጥያቄ እና መልስ ክፍል 99

    Play Episode Listen Later Dec 18, 2021 41:13


    የዛሬ ጥያቄዎች 1. ሳምሶን የተቀባ አመንዝራ ነው የሚለው ሀሳብ ይብራራልን። እግዚአብሔር የቀባው ሰው እንደ ሳምሶን ዐይነት ህይወት ነው የሚባለው ምን አይነት ሲሆን ነው? 2. የቃሉ ሙላት የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ነው የሚለውን ሀሳብ አብራራልን። 3. የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ከሌለ ለልጆቻችን ወንጌል ማድረስ አንችልም የሚለውን ሀሳብ አብራራልን። ወንጌል ሰምተው ሰዎች ወደ መዳን የማይመጡት ለዚህ ነው ማለት ነው? 4. ጌታ እየሱስ 30 ዓመት ለማገልገል መንፈስ ቅዱስ ስላልተሞላ ነው ወይስ ግዜው ስላልደረሰ? 5. ቃሉ ክርስቶስ ስለሆነ ቃሉ የሌለው ሰው ደስታ የለውም የሚለውን ሀሳብ አብራራልን።

    እርስ በእርስ መተናነጽ

    Play Episode Listen Later Dec 17, 2021 35:00


    ሐዋርያት አንድ ላይ በመሆን ይተናነጹ ነበር፣ ዛሬም በዘመናችን ቤተ ክርስቲያን እንድትናነጽ አንዳችን ለአንዳችን መጸለይ የወንድማችን ወይም የእህታችን ነገር ተስምቶን ልንሸካከም ይገባናል፣ እንዲሁም የእግዚኣብሔርን እውነት እየገለጽን በመካከላችን ያለ እውቀት ያሉትን በቃሉ እግዚአብሔርን ወደማወቅ እንዲደርሱ ማስተማር፣ እርስ በእርስ በመዋደድና በመከባበር አብረን የሰማዩን መንግስት እንደምንወርስ ሁልጊዜ ማሰብ ያስፈልገናል

    ያደገ ማንነታችን ክርስቶስን በመምሰል ሲገለጥ ባላደገው ማንነታችን ደግሞ ስጋችን ይገለጣል ምሳ 20:22 1ኛ ጵጥ 3

    Play Episode Listen Later Dec 17, 2021 9:17


    ያደገ ማንነታችን ክርስቶስን በመምሰል ሲገለጥ ባላደገው ማንነታችን ደግሞ ስጋችን ይገለጣል ምሳ 20:22 1ኛ ጵጥ 3

    የእግዚአብሔርን ተስፋ መውረስ

    Play Episode Listen Later Dec 17, 2021 39:36


    እግዚአብሔር ለቃሉ የታመነ ነው፣ እርሱ እስራኤላውያንን ሊያድን ሲመጣ ለአባቶቻቸው የገባውን ቃል ነበር የሚያመለክታቸው፣ የእምነት አባቶችም የተስፋይቱን ምድር እንደሚወርሱ የተናገራቸው አምላክ እግዚአብሔር ታማኝ መሆኑን ተቀብለው ምድሪቱን እንደሚወርሱ አምነው ነው የሞቱት፣ አንዳንድ ጊዜ መከራው በዝቶብን አልፈን ማየት ቢከብደን እንኳን እግዚአብሔር አደርጋለሁ ያለውን የሚያደርግን ምንም የማያቆመው ታላቅ አምላክ መሆኑን ልናምን ያስፈልገናል፣ Activity

    ያደገ ሰው ለሚወስነው ውሳኔ

    Play Episode Listen Later Dec 16, 2021 10:28


    ያደገ ሰው ለሚወስነው ውሳኔ ሁሉ የእግዚያብሔርን ሃሳብ የሚጠይቅ ሰው ነው ያላደገ ስው ግን ስዎች የሚሉትን ብቻ ይሰማል 1ኛ ሳሙ 14:36 ሮሜ 8:14 መሳ18:5-

    መኖር

    Play Episode Listen Later Dec 16, 2021 47:50


    ክርስትና በጨለማ ላለው ሕዝብ የሚመሰከው በመኖር ነው፥ ጌታ በቃሉ ስያስተምር፤ መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ ብሎዋል፣ ጌታ ሐዋርያትን በአፍ ከመመስከራቸውና ከመስበካቸው በፍት ክርስትናን ነረው እንድያሳዩ ነው የፈለገው፥ ክርስትና ኖረን በሕይወታችን የሚታይ መሆን አለበት፣ የጌታም ክብር ጎልቶ የሚታየው ያኔ ነው

    ሁሉን አድስ አደርጋለሁ ኢሳ 61፡3.

    Play Episode Listen Later Dec 16, 2021 63:35


    ኃጢያት ወደ ዓለም ሲመጣ ውርደት ይዞ ነው የመጣው፣ አዳምና ሕዋን ኃጢአትን በሰሩ ጊዜ ከእግዚአብሔር መንግሥት ጎሎዋል፣ውርደትን ለብሰዋል፣ መንፈሳዊ ውድቀት የሆነው በሰው ሕሊና፣ በሰው ልብ፣ በሰው አስተሳሰብ፣ በሰው አመለካከት ውስጥ ነው፥ ጌታ ኢየሱስ ስጋ ለብሶ ወደ ምድር የመጣው በኃጢያያት ምክያት ከአግዚአብሔር መንሥት የተለየውን የሰው ልጅ ወደ ክብሩ ለመመለስ ነው፤ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ ብሎ በቃሉ እንደ ተናገረ አምነው ለተከተሉት የሕይወት ተድሶ ለማድረግ ነው

    በእምነት ማደግ

    Play Episode Listen Later Dec 15, 2021 45:20


    አማኝ ከሁሉ በላይ የሚያስመካው የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አብሮነትና መገኝት ብቻ ነው እግዚአብሔር በምህረቱና በቸርነቱ በህይወታችን ከሚያደርገው በጎነቱ የተነሳ የጊዜውን ነገር ብቻ እየተመለስ የምንኖር ሳይሆን በእምነት እንድናድግ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው

    ያደገ ሰው የውስጡን ንጽህና

    Play Episode Listen Later Dec 15, 2021 11:25


    ያደገ ሰው የውስጡን ንጽህና ግድ ይለዋል ያላደገ ሰው ደግሞ ስው የሚያየው የውጭው ማንነቱ ግድ ይለዋል መዝ 51:10 ዘፍ 6:5 ዘፍ 8:21 ማቴ 5:8

    የእግዚአብሔር ነገር በእምነት ነው

    Play Episode Listen Later Dec 15, 2021 40:33


    እምነት ማለት በእግዚአብሔር ዘንድ የሚደረግልንን አይናችን ሳያይ ጌታ በተናገረን ውስጥ ሆነን ሁሉን ለርሱ በመተው እንደሆነልን እንደተደረገልን አምነን በሰላሙ ውስጥ ማረፍ ነው

    በጌታ ያደገ ማንነት እና ያላደገ ማንነት

    Play Episode Listen Later Dec 14, 2021 11:32


    በጌታ ያደገ ማንነት እና ያላደገ ማንነት ገላ 4 ሉቃ 11:5-13 ዕብ 4:16

    ያደገ ሰው ፀሎት እና ያላደገ ሰው ፀሎት

    Play Episode Listen Later Dec 13, 2021 10:24


    ያደገ ሰው ፀሎት እና ያላደገ ሰው ፀሎት መዝ 32:6 ኤር 2:27 ሉቃ 22:46 መዝ 11

    ስለ መለኮት ጥበቃ

    Play Episode Listen Later Dec 13, 2021 39:20


    እግዚአብሔር ያለውን የምንሆነው በመለኮት ጥበቃ ውስጥ እንዳለን አይናችን ሲበራ ብቻ ነው፣ ያለዚያ እንታወካለን፣ ለፈቃዱ ወይም ለተጠራንበትም መኖር አንችልም፣ አይናችን ሲበራ ግን እራሳችንን ከሐጢያት የምንጠብቅበት ወይም ክፉውን የምንጸየፍበትና እግዚአብሔርን በመፍራት የምንኖርበትን ማስተዋልና ጥብብን የተቀበልነው ከመለኮት መሆኑን እንረዳለን፣ በእርሱም አርፈን እንኖራለን

    ወንጌል

    Play Episode Listen Later Dec 13, 2021 26:58


    ሰማያዊ ዜግነትን ሰው የሚያገኝው ወንጌልን ሰምቶ ሲያምን ብቻ ነው ወንጌል ሁሉም አካል የሚሰራው ስራ ሲሆን አንዱ በመሄድ ሌላው በጸሎት በገንዘብ በሚያስፈልገው ሁሉ ይህን የምስራች በማድረስ ሰዎች ሲድኑ ደስ መሰኝት ለተቸገሩ መድረስ ነው

    የሰው ልጅ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን መጥቷል

    Play Episode Listen Later Dec 13, 2021 45:27


    የውስጥ ጥማት ካለ ለኔ አይሆንም የምንለው ምንም ነገር የለም፣ እግዚአብሔር ዘኪዮስን በጊዜው እንደጎበኘው፣ እኛ ክርስቶስን ለማግኘት ፍላጎትና ጥማት ይኑረን እንጂ ጌታ ማንንም አያሳፍርም፣ እርሱን ለማየት ብዙ ነገሮች በዙሪያችን ቢጋርዱን እንኳን የልባችንን መሻት የሚያውቅ አምላክ እግዚአብሔር በጊዜው በዙሪያችን ከጋረዱን ነገሮች አልፎ ወደእኛ ይመጣል

    እግዚአብሔር መንገድ አለው

    Play Episode Listen Later Dec 13, 2021 23:08


    እግዚአብሔር በማእበል በወጀብ ውስጥ መንገድ አለው ክብሩን ለመግለጥ እምነታችንን ለመጨመር እንባችንን ለመጥረግ የጎበጠ ነገራችንን ቀና ለማድረግ ለማስጣል ለማዳን ለመባረክ መንገድ አለው

    ጥያቄ እና መልስ ክፍል 98

    Play Episode Listen Later Dec 12, 2021 46:49


    የዛሬ ጥያቄዎች 1. ምሳሌ 31፡11 መንፈስ ቅዱስን የሚያሳዝን ሰው ይለፋል ፍሬ የለውም የሚለውን ሀሳብ አብራራልን። 2. መዝሙር 53፡1 የሚጸጸት ህይወት ከሌለን የንስሀ ፍሬ የለንም የሚለው ሀሳብ አብራራልን። 3. ምሳሌ 16 ለትውልድ የምናተርፈው ነገር ምንድን ነው? 4. ምሳሌ 31፡17 የውሳኔ ሰው መሆን ያስፈልገናል የውሳኔ ሰው ያልሆነ ግን ህይወት አደጋ ላይ ነው ያለው ለእርሱ ብቻ ሳይሆን በአካባቢው ላሉ ጭምር መሚለው ሀሳብ ይብራራልን። 5. ወደ እግዚአብሔር ስቀርብ እንደ ማይገባው ሰው መኦን አለበት የሚለው ሀሳብ ይብራራልን። 6. ምሳሌ 31፡18 አመስጋኝ ሰው መብራቱ አይጠፋም የሚለው ሀሳብ ይብራራልን። 7. የአንዳንድ ሰው መብራት የሚታየው በቀን ብቻ ነው የሚለው ሀሳብ ይብራራልን። ይህ ብርሀን በቀን ብቻ እንደሚበራልን በማታ እንደማይበራ እንዴት ነው የምናውቀው? 8. 2ኛ ነገሥት 8 እግዚአብሔር የሚያየን ቃሉን እንዴት እንደ ተቀበልን ነው እንጂ ምን እንዳደረግን አይደለም የሚለው ሀሳብ ይብራራልን።

    ጥያቄ እና መልስ ክፍል 97

    Play Episode Listen Later Dec 11, 2021 42:24


    የዛሬ ጥያቄዎች 1. የጌታ ወዳጆች ሀጢያተዮች ነበሩ የእኛስ ወዳጆች እነማን ናቸው? 2. እግዚአብሔር በተለያየ ጎዳና ሊያገኘን ይችላል። ጸሎታችንንም ሊመልስ ይችላል ነገር ግን ያልተገኘ የህይወት ክፍል ሊኖረን ይችላል የሚለው ሀሳብ ይብራራልን። 3. ማቲዮስ 3፡16-17፤ 4፡1 ለእግዚአብሔር ለመገኘት ከጥምቀት በሗሏ በመስቀል ህይወት ማለፍ አለብን ወይ? 4. መኋልየ መኋልይ 4፡12 ምንጩን የምንደፍነው ራሳችን ነን ነገር ግን እግዚአብሔር ይከፍተዋል የሚለው ሀሳብ ይብራራልን። 5. በህይወታችን ቅጣት ሲመጣ እንዴት ነው የምናውቀው? ይህንን እኛ ነን ወይስ ሌሎች ናቸው የሚይውቁት? ቅጣትስ ለምንድን ነው የሚመጣው? 6. 1ኛ ጥሞቴዎስ 2፡15 ይብራራልን። ምሳሌ 31፡15 ማለዳ የሚለው ግዜን ነው ወይ የሚያመለክተው? 7. ምግብ አብልታ ወደ ተግባር ታሰማራቸዋለች የሚለው ሀሳብ ቢብራራልን? 8. ኤፌሶን 2፡5 በአደገ ማንነታችን ጸጋን የምንፈልገው ከሀጢያት ለመላቀቅ ነው ይላደገው ማንነታችን ግን ጸጋን ለመሸፈን እንፈልገዋለን ይህንን ወደ እኛ ህይወት አምጥተ አብራራልን።

    የጥሞና ጊዜ በግል ሕይወታችን

    Play Episode Listen Later Dec 10, 2021 28:07


    የጥሞና ሕይወት የተለማመዱ ስዎች የእግዚአብሔርን ቅድስና ይለማመዳሉ የቅድስናውን ሕይወት ይካፈላሉ ከብዙ ነገር እራሳቸውን ይጠብቃሉ። ቅድስና ከእግዚአብሔር የምንካፈለው ነው በራሳችን ይምናመጣው አይድለም፤ መጽደቅ አንድ ግዜ ነው፡ ቅድስና ግን እለት እለት ይምንለማመደው ነገር ነው፤ ጽድቅ የተገለጠው በጌታ በእየሱስ ክርስቶስ ነው።

    የእግዚአብሔር ቸርነት

    Play Episode Listen Later Dec 9, 2021 56:46


    እግዚአብሔር ያለውን የሚያደርግ ሉአላዊ አምላክ ነው ቅንነት ፊቱን ታየዋለች እግዚአብሔር መግቢያው የቀና ልብ ነው በረከቱ ወደ እኛ የሚመጣው በመታዘዝ ነው

    እግዚአብሔር አስቀድሞ ይናገራል

    Play Episode Listen Later Dec 9, 2021 34:53


    ከሰማይ የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ህይወታችንን ኑሮአችንን ዛሬንና ነገአችንን ያቀናል ጌታ አስቀድሞ በህይወታችን በተናገረው ውስጥ እናልፋለን መልካሙን ገድል እንጋደላለን

    ጥያቄ እና መልስ ክፍል 96

    Play Episode Listen Later Dec 5, 2021 49:49


    የዛሬ ጥያቄዎች 1. ጌታ የሰጠን ፍቅር እሱን ብቻ እንድንወድ ሳይሆን የእርሱ የሆኑትን ጭምር እንጂ የሚለውን ሀሳብ አብራራልን። 2. የእርሱ የሆኑትን መውደድ የምንቸገረው ለምንድን ነው? 3. 1ኛ ቆሮንቶስ 1፡4 ያደገ ሰው በሞተ ፍቅር ላይ ህይወትን ይዘራር የሚለውን ሀሳብ አብራራልን። 4. የእግዚአብሔር እረፍት በእኛ የሚሆነው እሱ በአለን ውስጥ ስንገኝ ነው የሚለውን ሀሳብ አብራራልን። 5. ራሳችንን እግዚአብሔር በተናገረን ካላየን መስኮት እንደሌለው ቤት ነው የምንሆነው የሚለው ሀሳብ ይብራራልን። 6. ዮሐንስ 5፡5 መንፈሳዊ ነገር ስንሆን አስመስለን የምንለው ነገር አለ እና ይህ ይብራራልን። 7. መኋልየ መኋልይ ዘሰለሞን 4፡12-16 የመከራ እና የድርቀት ንፋስ ካለመጣ ነገራችን አይከፈትም ወይ?

    ጥያቄ እና መልስ ክፍል 95

    Play Episode Listen Later Dec 4, 2021 40:24


    የዛሬ ጥያቄዎች 1. ምሳሌ 30፡11-12 በወላጆቻቸው የተጎዱ ልጆች የእግዚአብሔር በረከት እንዲያገኛቸው እንዴት ነው እንደዚህ ዐይነት ልጆችን ማገልገል የምንችለው? 2. በግልፅ የሚደረግ ፀሎትና በስውር የሚደረግ ፀሎት ብታብራራልን? እንዴት ነው እንደዚህ ዐይነቶች ፀሎት መፀለይ የምንችለው? 3. ምሳሌ 31፡1-5 ልጅን በማሳደግ ውስጥ ልጆች በሚያልፉበት መንገድ የወላጆች ድርሻ በተመለከተ ምን ትመክረናለህ? 4. ከውጪ ያየነውንወደ ቤተ ክርስትያን ስላመጣነው ምን ትመክረናለህ? 5. ምሳሌ 31፡13 በማጉረምረም እና በማረም ላይ ልጅን በማሳደግ ላይ ያለው ልዩነት ምንድን ነው?

    የቤተክርስቲያን ዋና ተልዕኮዎች

    Play Episode Listen Later Dec 3, 2021 24:27


    የቤተክርስቲያን ዋና ተልዕኮ የእግዚአብሔርን በጎነት መናገር፣ መንፈሳዊ ቤት ሆኖ መሰራትና መንፈሳዊ መስዋዕትን ማቅረብ ነው፣ ታላቁ ትዕዛዝ ደግሞ አምላካችንን በፍጹም ልባችን ነፍሳችንና ሃሳባችን መውደድና ባልንጀራችንን ደግሞ እንደራሳችን መውደድ ነው፣ ጌታን መውደዳችንን የመንገልጸው ከአላማው ጋር በመተባበርና ለቃሉ በመታዘዝ ሲሆን በምድር ሲያስቀምጠን ትልቁ አላማው ደግሞ ወንጌልን ለፍጥረት ማድረስ ነው፣ ባልንጀራችንን እንደራሳችን እድርገን መውደዳችንን የምንገልፀው ለባልንጀራችን መልካም ነገርን በማድረግ ሲሆን ሰውን ሁሉ ወደ ዘለአለም ህይወት ከመምራት የበለጠ ደግሞ ምንም መልካም ነገር የለም፣ አማኞች ለዚህ ታላቅ ተልዕኮ ሁልጊዜ የተጋን እንድንሆን ጌታ ይርዳን፣

    የጥሞና ጊዜ,,,ካለፈው የቀጠለ

    Play Episode Listen Later Dec 3, 2021 23:36


    የጥሞና ጊዜ በእግዚአብሔር ላይ የማረፍ ህይወት ነው የጥሞና ጊዜ የለመዱ ሰዎች ፊቱን ይናፍቃሉ በእግሩ ስር መሆን ይወዳሉ ደስታና እረፍት በመንገዳቸው ነው አይናወጡም ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ስር ናቸው

    እግዚአብሔር በተናገረው ውስጥ ራስን ማግኘት

    Play Episode Listen Later Dec 3, 2021 35:37


    የአንድ አማኝ መንፈሳዊ ሀብቱ ባለበት ሁኔታ ውስጥ ራስን በእግዚአብሔር ቃል ተስፋ በመለኮት ሀሳብ ውስጥ ማግኘቱ ነው

    GMT20211201-012925_Recording

    Play Episode Listen Later Dec 1, 2021 34:05


    Claim Voice of Truth and Life

    In order to claim this podcast we'll send an email to with a verification link. Simply click the link and you will be able to edit tags, request a refresh, and other features to take control of your podcast page!

    Claim Cancel