Mission Europe – Mission Berlin | ጀርመንኛ መማር | Deutsche Welle

Follow Mission Europe – Mission Berlin | ጀርመንኛ መማር | Deutsche Welle
Share on
Copy link to clipboard

Mission Europe ለጀማሪዎች የተዘጋጀ የቋንቋ ትምህርት ሲሆን ፦ Mission Berlin ፦ Misja Kraków እና Mission Paris የሚሰኙትን ልብ ሰቃይ ወንጀል ነክ ታሪኮችን አካቶዋል። ወደ ቋንቋው ዓለም በመዝለቀ የፖላንድኛ፣የ ጀርመንኛ ወይም የፈረንሳይኛ ቋንቋ ይማሩ።

DW.COM | Deutsche Welle


    • Feb 25, 2010 LATEST EPISODE
    • infrequent NEW EPISODES
    • 5m AVG DURATION
    • 25 EPISODES


    More podcasts from DW.COM | Deutsche Welle

    Search for episodes from Mission Europe – Mission Berlin | ጀርመንኛ መማር | Deutsche Welle with a specific topic:

    Latest episodes from Mission Europe – Mission Berlin | ጀርመንኛ መማር | Deutsche Welle

    Mission Berlin 24 – ሰዐቱ ይሮጣል

    Play Episode Listen Later Feb 25, 2010 5:00


    አና በ 1961 ዓ ም የደበቀችውን የብረት ሳጥን መልሳ ታገኘዋለች። ስለዛገ ግን መክፈት ያቅታታል። ሲሳካላት ደግሞ ያረጀ ቁልፍ ታገኛለች። የሚስጥር ቁልፍ ይሆን? ሰዐቱ ይሮጣል። አና የብረት ሳጥኑን መክፈት አለባት። ተጫዋቹ ግን ሌላ ሰው ባለበት ማህሌቱን እንዳትከፍት ያስጠነቅቃታል። ሳጥኑ ውስጥ አሮጌና የዛገ ቁልፍ ታገኛለች። ቀይ ለባሿን ሴት ለማሸነፍ አሁን ቶሎ ብላ ወደ 2006 ዓ ም መመለስ አለባት። ለዚህ ግን በቂ ጊዜ ይቀራት ይሆን?

    Mission Berlin 25 – በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ

    Play Episode Listen Later Feb 25, 2010 5:00


    ሰዐቱ እየጠበበ ነው። አና ፓውልን መሰናበት አለባት ወደ ህዳር 9 2006 ዓ ም ለመመለስ። ተልኮዋን ለማሳካት 5 ደቂቃዎች ብቻ ናቸው የቀሯት። ይበቋት ይሆን? ተጫዋቹ አና ያለውን ግርግር ተጠቅማ እንድትጠፋ ይመክራታል። አና ግን ፓውልን ሳትሰናበት መጓዝ አትፈልግም። የጨዋታውን ውጤት ስትመዘግብ የዛገው ቁልፍ እንቆቅልሹን ለመፍታት የሚያስፈልጋት አንደኛው ቁልፍ እንደሆነ ትደርስበታለች። ሌላኛው ደግሞ ሙዚቃው ነው። ግን መጥፎውን ነገር እንዳይከሰት ለማድረግ በሰዐቷ ትደርስ ይሆን? ተልኮዋን ለማሳካት 5 ደቂቃዎች ብቻ ናቸው የሚቀሯት።

    Mission Berlin 26 – የጊዜ ተሞክሮ

    Play Episode Listen Later Feb 18, 2010 5:00


    ወደ አሁን ስንመለስ አና ከፓውል ጋር የድሮውን የሚያስታውሰውን ነገር ለመዝጋት ትሞክራለች። ግን የሚስጥር ቁልፉ ይጠፋታል። አና ሙዚቃውን ትከተላለች። ቀይ ለባሿ ሴት ብቅ ትላለች። ሀላፊዋ የ አናን እቅድ ግብ ከመግባቱ በፊት ታበላሽ ይሆን? አና ወደ ጥንት ትመለሳለች። ፓውልን የዛገውን ቁልፍ ታሳየዋለች የድሮውን የሚያስታውሰውን ነገር እንዲቀረቅርበት። ግን ለዛ የሚስጥር ቁልፉ ያስፈልጋታል። እሱ ደሞ የላትም። አና የዳህፌግስን ስም በመስጠት ለመዝጋት ተሞክራለች። ባለቀ ሰዐት ቀይ ለባሿ ሴት ብቅ ትልና ቁልፉን እንድትሰጣት ትጠይቃለች። አና ቁልፉን ማሽን ውስጥ ትከትና የሚስጥር ቁልፉን ትሰጣለች። ቀይ ለባሿ ሴት የድሮውን የሚያስታውሰውን ነገር እንዳይበላሽ ማድረግ ትችል ይሆን ወይስ እሷም እንደ ማሽኑ ታሪክ ሆና ትቀራለች?

    Mission Berlin 23 – እስከ በኋላ

    Play Episode Listen Later Feb 18, 2010 5:00


    አና በሞተር ሳይክል ወደ በርንአወር መንገድ ትወሰዳለች። የሚወስዳት ሰው ኤምረ ኦጉር ይባላል። መልካም ጊዜ በበርሊን ይመኝላታል። ግን ከቀይ ለባሿ ሴት ለማምለጥና የብረቱን ሳጥን ለማግኘት ይበቃት ይሆን? ተጫዋቹ አና ጊዜ ስለሌላት ወደ በርንአወር መንገድ የሚወስዳት ሰው እንድትፈልግ ይመክራታል። አናን በሞተር ሳይክል አንድ ወጣት ሰውዬ ፤ የበኋላው መርማሪ ኤምረ ኦጉር ይወስዳታል። ከዚያም አና ሀይድሩንና ፓውልን ስታገኝ ቀይ ለባሿ ሴት ብቅ ትላለች። ፓውልና የሀይድሩን ባል ሊያባርሯት ይችላሉ። ይህ በእንዲህ እንዳለ አና ማህሌቱን ለማምጣት መንገድ ትጀምራለች። ግን ማህሌቱ ከብዙ አመታት በኋላ አሁንም እዚያው ይሆን ያለው?

    Mission Berlin 22 – እርምጃ ለመውሰድ ተዘጋጂ

    Play Episode Listen Later Feb 18, 2010 5:00


    አና ወደ በርሊን 1989 ዓ ም ፤ በግንቡ መፍረስ የተነሳ ትልቅ ደስታ ወደሚታይበት ከተማ ትመለሳለች። በዚህ ግርግር ተጋፍታ ማህደሩን መውሰድ አለባት። ይሳካላት ይሆን? ልክ አና ወደ 1989 ዓ ም ልትጓዝ ስትል ጥቁር ኮፍያ የሚያደርጉት ብቅ ይላሉ። ቀይ ለባሿ ሴት አናን እንዲፈልጉ ትዕዛዝ ትሰጣለች። በህይወት እንዲያመጧት! አና ግን የድሮውን ነገር በሚያስታውሰውን ነገር በሰዐቷ የበርሊን ግንብ ወደ ፈረሰበት ቀን ትመለሳለች። የብራንድቡርገር በር ጋር ግርግር ውስጥ ቆማለች። ግን ወደ በርንአወር መንገድ መሄድ አለባት። 30 ደቂቃዎች ብቻ ናቸው የቀሯት። ግን ከዚህ ግርግር በሰዐቷ ተከፋፍላ ከነበረችው ከተማ መውጣት ትችል ይሆን?

    Mission Berlin 21 – አዲሱ ዕቅድ

    Play Episode Listen Later Feb 18, 2010 5:00


    አና ወደ 2006 ዓ ም ትመለሳለች። ቀይ ለባሿ ቄስ ካቫሊርን ትጠልፋለች። አና ቄሱ የት እንዳለ ስላላወቀች ወደ ህዳር 9 1989 ዓ ም ትጓዛለች። አና ወደ 2006 ዓ ም ስትመለስ ፓውል ቄሱ የት እንዳለ እንደማይታወቅ ይነግራታል። ፓውል የበለጠ ስለ ቄሱና የድሮውን ስለሚያስታውሰው ነገር ሳያውቅ አይቀርም። ግን ስለዚህ ለማውራት ጊዜ አይበቃም። አና ወደ ህዳር 9 1989 ዓ ም ምሽት ለመጓዝ ፍቃደኛ ነች። እዛም ስትደርስ በግንቡ መፍረስ የተነሳ በደስታ የምታከብር ከተማ ታገኛለች። በዚህ ግርግር ተደብቃ ማህደሩን ለመውሰድ ትሞክራለች።

    Mission Berlin 20 – ከጊዜ ወደ ጊዜ

    Play Episode Listen Later Feb 18, 2010 5:00


    አና አሁንም የእንቆቅልሹን መልስ አልደረሰችነትም። RATAVA የትኛውን ክስተት ሊያሰናክል ይፈልጋል? አና ወደ 2006 ዓ ም ከተመለሰች በኋላ ወደ 1989 መጓዝ አለባት። ግን ጉዞው ምን ያህል አደገኛ ነው? አና ወደ 2006 ዓ ም ከመመለሷ በፊት ከፓውል ጋር በደስታ ትሰናበታለች። 35 ደቂቃዎች ብቻ ናቸው አላማውን ለማሳካት የሚቀሯት? ተጫዋቹና አና አሁንም የእንቆቅልሹን መልስ ለማግኘት ይሞክራሉ። ለምሰሌ RATAVA የትኛውን ታሪካዊ ክስተት ሊያሰናክል እንደሚፈልግ። ወዲያው ሽብር ፈጣሪዎቹ የግንቡ ግንባታ ሳይሆን የግንቡን መፍረስ አንደሚፈልጉ ይደርሱበታል። ተጫዋቹ ወዲያው አና ወደ 1989 ዓ ም እንድትጓዝ ይወስናል። ግንቡ ሲፍረስ አና በቦታው እንድትገኝ።

    Mission Berlin 19 – ፍቅር በቀዝቃዛው ጦርነት

    Play Episode Listen Later Feb 18, 2010 5:00


    የቀሩት 40 ደቂቃዎች ናቸው። አናና ፓውል ቀይ ለባሿን ሴት አምልጠው ምዕራብ ጀርመን ይገባሉ። ፓውል ነገሮቹን ግራ የሚያጋባ ያደርጋል። ከአና ፍቅር እንደያዘው ይነግራታል። ዕድል ወይስ እንቅፋት? አና ተልኮዋን ለመወጣት ምስራቅ ጀርመን መግባት አለባት። ግን ምዕራብ ነው ያለችው። ሌላም ችግር አለ። በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ፓውል ከሷ ፍቅር እንደያዘው ይነግራታል። ተልኮዋን እንድታቋርጥ ይፈልጋል። ተጫዋቹ ደግሞ ተመልሳ ወደ 2006 ዓ ም እንድትመለስ ይፈልጋል። በተጨማሪም አዲስ አላማ እንድታዘጋጅ ይፈልጋል። የቀሩት 35 ደቂቃዎች ይበቃቸው ይሆን አላማውን ለማሳካት?

    Mission Berlin 18 – የተደበቀው ማህደር

    Play Episode Listen Later Feb 18, 2010 5:00


    አና ቀይ ለባሿ ሴት የ RATAVA ሀላፊ መሆኗን ትደርስነታለች። 45 ደቂቃዋች ብቻ ናቸው የቀሯት። ለአና ወሳኝ ምንጭ አሁን ቀይ ለባሿ የደበቀችው ማህደር ነው። አና ከተደበቀበት ማውጣት ትችል ይሆን? ሀይድሩን ፓውልና አና ወደ በርንአወር መንገድ ሲሄዱ የሀይድሩን ባል ሮብርት ያገኙታል። እሱም ከተማው በሙሉ በወታደር እንደተሞላ ይነግራቸዋል። ከዛም በላይ የሚያስፈራው ግን ጥቁር ኮፍያ ያደረጉት ሞተር ሳይክል ነጂዎች ጉዞ መጀመራቸው ነው። ኣራቱም አንድ ቢራ የሚመረትነት ቤት ይደበቃሉ። ቀይ ለባሿ ሴት እዛ ብቅ ስትል ፓውል ለአና የ RATAVA ሀላፊ መሆኗን ይነግራታል። አናና ፓውል ይከታተሏታል። እሷም እንዴት ብላ አንድ የብረት ማህደር እምድር ቤት እንደምትደብቅ ያያሉ። እነሱም ይህንኑ ለመውሰድ ሲሉ ይረበሻሁ። ስለዚህ ማህደሩን ሌላ ቦታ መደበቅ አለባቸው። ተጫዋቹ እንዴት ብለው ማህደሩን በኋላ ሊወስዱ እንደሚችሉ ዘዴ አለኝ ይላል። ግን የቀሩት 40 ደቂቃዎች ይበቃቸው ይሆን?

    Mission Berlin 17 – የአጥር ግንባታ

    Play Episode Listen Later Feb 18, 2010 5:00


    50 ደቂቃዋች ይቀራሉ። ተጫዋቹ ገንዘብ ተቀባይዋን ማመን እንደሚሻል በሙሉ ሀላፊነት ይወስናል። በሬድዮ ምስራቅ ጀርመን አጥሩ ጋር ስለቆሙ ወታደሮች ይወራል። ይኼ የ RATAVA መልስ ይሆን? አና እስካሁን ገነዘብ ተቀባይዋ ሀይድሩን ድራይ እንደሆነች አላወቀችም። ተጫዋቹ ለርዳታ ፍቃደኛ የሆነችውን ሴት ምንም እንኳን ወንድሟ ፓውል አጠራጣሪ ቢሆንም አና እንድታምናት ይመክራታል። ሆኖም እሱ አና ሞተር ሳይክል ነጂዎቹን እንድታመልጥ እንደሚረዳ ፍቃደኛ ይሆናል። በኋላም አና ፤ፓውልና ሀይድሩን የምስራቅ ጀርመን ወታደሮች እንዴት የሚዋጋ ሽቦ መንገድ ላይ እንደሚያስቀምጡ ያያሉ። ተጫዋቹ አናን የግንብ ግንባታው ስራ ማስጀመሪያ እንደሆነ ይነግራታል። አና ጀርመንን ለማዳን 45 ደቂቃዋች ብቻ ናቸው የቀሯት።

    Mission Berlin 16 – የድሮ ጓደኛ

    Play Episode Listen Later Feb 18, 2010 5:00


    በ 1961 ኛው ዓ ም አናን የታጠቁት ሞተር ሳይክል ነጂዋች ያባርሯታል። በዚህ አስፈሪ ጊዜ አንዲት የማትታወቅ ሴት ትረዳታለች። ግን ለምን ትረዳታለች? አናስ ልታምናት ይገባል? ሞተር ሳይክል ነጂዎቹ አናን ይከታተሏታል። እሷም ወደ ምግብ መሸጫ መደብር እሸሻለች። የሱቁ አለቃ እየዘጋ እንደሆነ ሲነግራት አንዷ ተቀጣሪ አና ጓደኛዬ ነች ትላለች። ገነዘብ ተቀባይዋ አናን ወደ ቤቷ ትወስድና የ ት/ ቤት ጓደኛዋ ነኝ ትላለች። አና ትጠራጠራለች ግን ተጫዋቹ አና ሴትዬዋን ማመን እንዳለባት ይነግራታል። አና የ ገነዘብ ተቀባይዋ ቤት የሴትየዋን ወንድም ፓውል ቪንክለር ትተዋወቃለች።

    Mission Berlin 15 – የጊዜ ጉዞ

    Play Episode Listen Later Feb 18, 2010 5:00


    አና ከተከፈለችው ምስራቅ በርሊን ወደ ምዕራብ በርሊን መመለስ አለባት። ግን ይህ ብቻ አይደለም። በ 55 ደቂቃዎች ውስጥ RATAVA ምን እንደሆነ ጭምር፤ የበርሊን ግንብ ምስረታ ወይስ ፍርስ? አና 1961 ኛው ዓ ም እንደደረሰች ወደ ካንት መንገድ ለመሄድ ትሞክራለች። ይህ ግን ሊሳካ አይችልም። ምክንያቱም የDDR መንግስት የግንብ ግንባታውን ስለጀመረና አና ደግሞ በምስራቁ በኩል ስላለች። ግን የካንት መንገድ ምዕራብ በርሊን ነው የሚገኘው። ጨዋታውን እንደ አዲስ ካደሱ በኋላ አናና ተጫዋቹ ሁለት ታሪካዊ ክስተቶች ያገኛሉ፦ የ RATAVA አላማ ሊሆን የሚችሉ። የበርሊን ግንብ ምስረታ ወይስ ፍርሰት። ተጫዋቹና አና ይህንን ለማወቅ 55 ደቂቃዎች ብቻ ነው የሚቀራቸው።

    Mission Berlin 13 – የእግዚያብሄር እርዳታ

    Play Episode Listen Later Feb 18, 2010 5:00


    ቤተ ክርስትያኒትቱ መረጃ ለመሰብሰብ ትክክለኛ ቦታ ሳትሆን አትቀርም። ቄሱ ለአና የሙዚቃው ቅንብር የድሮውን ነገር የሚያስታውስ ቁልፍ እንደሆነ ያብራራላታል።ግን ምን አይነት መሳሪያ ማለቱ ነው? ጨዋታው እንደ አዲስ ከተጀመረ በኋላ አና ከቀይ ለባሿ ሴት ታመልጣለች። ቄሱ ለአና መርማሪ ኦጉር እንደቆሰለና ሆስፒታል እንደተኛ ይነግራታል። ለአናም የሙዚቃውን ቅንብር በድጋሚ ያሰማትና የሙዚቃው ኖት አደራደር D A C H F E G የድሮውን ነገር የሚያስታውሰን ቁልፍ እንደሆነ ያብራራላታል። ይኼ ድል ለተጫዋቹና ለአና የአስር ደቂቃዎች ሽልማት ያስገኛቸዋል። ግን ጊዜው ይበቃቸው ይሆን?

    Mission Berlin 12 – የ ቤተ ክርስትያን መዝሙር

    Play Episode Listen Later Feb 18, 2010 5:00


    አና 65 ደቂቃዎች ይቀሯታል። የመጫወቻው ቀፎ የቤተ ክርስትያኑ ኦርጋን አካል መሆኑን ትደርስበታለች። ቀይ ለባሿ ሴት ብቅ ትልና ከአና ቁልፍ ትጠይቃለች። ግን ምን አይነት ቁልፍ? የቤተ ክርስትያኑ ኦርጋን ከመጫወቻው ቀፎ ጋር አንድ አይነት የሙዚቃ ቅንብር ይጫወታል። አና ቀረብ ብላ የቤተክርስትያን አገልጋዩ ለጎብኝዎች የሚለውን ታዳምጣለች። ኦርጋኑ መታደሱን፤ የበርሊኑ ግንብ ከተሰራ በኋላ ግን ኦርጋኑ አንድ አካል እንደሚጎለው ይናገራል። አና የመጫወቻው ቀፎ የቤተ ክርስትያኑ ኦርጋን አካል መሆኑን ይገባታል። ኦርጋኑ መጫወት ሲጀምር አንድ በር ይከፈትና ቀይ ለባሿ ሴት ፊት ለፊቷ ትቆማለች። አና አንዱን ህይወቷን ታጣለች። የቀራትም 60 ደቂቃዎች ብቻ ነው።

    Mission Berlin 11 – ፈጣን ምግብ

    Play Episode Listen Later Feb 18, 2010 5:00


    አና ምግብ ከፓውል ጋር እየበላች ስለሚገርመው አረፍተ ነገር ፤ "In der Teilung liegt die Lösung. Folge der Musik!" ታወራለች። እሱም አደጋውን ያውቅና ወደ ቄስ ካቫሊር ጋር ይልካታል። ግን ይኼ ትክክለኛው መንገድ ነው? ፓውል የመጫወቻ ቀፎውን ጠግኗል። ግን የሙዚቃውን ቅንብር እስከ መጨረሻው ለማጫወት አንድ ነገር ይጎለዋል። አና ስለሚያስደንቀው መልዕክት ትነግረዋለች "In der Teilung liegt die Lösung. Folge der Musik!" ፓውል የመጫወቻ ቀፎውን ይሰጣትና ወደ ቄስ ማርኮስ ካቫሊር ጋር ጌትሰማኔ- ቤተ ክርስትያን ይልካታል። ተጫዋቹ ይኼ ቤተ ክርስትያን የምስራቅ ጀርመን (DDR) መንግስት ተቃዋሚዎች መገናኛ ቦታ እንደነበር ለአና ይነግራታል።

    Mission Berlin 10 – መውጫ የሌለው መንገድ

    Play Episode Listen Later Feb 18, 2010 5:00


    ተጫዋቹ እ ኤ አ ነሐሴ 13 1961 የበርሊኑ ግንብ የተሰራበት ቀን እንደሆነና ህዳር 9 ደግሞ ግንቡ የፈረሰበት ቀን እንደሆነ ይደርስበታል። የአና ተልኮ ከነዚህ ቀናቶች ጋር የተያያዘ ነው። አና ምን ማድረግ ትችላለች? ፓውልና አና ካድቬ ወደሚባል ገበያ አዳራሽ ከቀይ ለባሿ ሴት እየሸሹ ነው። የገበያ አዳራሹ አና የጨዋታዋን ውጤት የምታስቀምጥበት ቦታ ነው። ተጫዋቹ እ ኤ አ ነሐሴ 13 1961 የበርሊኑ ግንብ የተመሰረተበት ቀን እንደሆነና ህዳር 9 ደግሞ ግንቡ የፈረሰበት ቀን እንደሆነ ለአና ያብራራል። አና የተልኮዋ ሙሉ መልስ ከበርሊን መገንጠል ጋር የተያያዘ እንደሆነ ይገባታል።

    Mission Berlin 09 – ያልተሟላ ጥቆማ

    Play Episode Listen Later Feb 18, 2010 5:00


    አና ከቲያትር ቤቱ ትጠፋለች። ግን ቀይ ለባሿ ሴት የፓውል ሱቅ እስከምትገባ ድረስ ትከታተላለች። በሀይድሩን እርዳታ አማካኝነት አና ማምለጥ ትችላለች። እንቆቅልሹን ለመፍታት ሙሉ መረጃ የላትም። የተቀረውን ከየት ታገኝ ይሆን? መርማሪ ኦጉር አናን ከጊዜው ሽብር ፈጣሪዎች ፤ RATAVA እንድትጠነቀቅ ይነግራታል። ወደ ሰዐት መሸጫው ስንመለስ፤ ፓውል ቪንክለር የተጠገነውን የመጫወቻ ቀፎ ያሳያታል። የ ፍሪድሪክ ኦጉስት ዳህፌግ "Nostalgie" የሙዚቃ ቅንብር ትጫወታለች። "Unsere Melodie, Anna", ይላል ፓውል። ግን አና ምንም አይገባትም። በድንገት ቀይ ለባሿ ሴት ብቅ ትልና ተኩስ ትከፍታለች። ሀይድሩን ድራይ በቦታው ትገኝና ፓውልና አና ማምለጥ እንዲችሉ ታደርጋለች። አና አሁን ሁለት መረጃ ነጥቦች አግኝታለች። እ ኤ አ ነሐሴ 13 1961 እና ህዳር 9። ግን የትኛው አመት ነው?

    Mission Berlin 08 – ያልተዘጋ ሂሳብ

    Play Episode Listen Later Feb 18, 2010 5:00


    ኦጉር ከቀይ ለባሿ ጋር በተከፈተው የተኩስ ልውውጥ ይቆስላል። ለአናም ስለ RATAVA ታሪካዊ ክስተት ይገልፅለታል። እንደምንም ብሎ እ ኤ አ ህዳር 9 ይላታል። ግን በየትኛው አመት? መርማሪ ኦጉር አና ቲያትር ቤት እንደተደበቀች ይገምትና እንድታመልጥ ይገፋፋታል። ቀይ ለባሿ ሴት አና ላይ ትተኩስና አና አንድ ህይወት ታጣለች። ጨዋታው እንደገና ከተጀመረ በኋላ ኦጉር ለአና ፤ በቡድን ያሉ የጊዜው ሽብር ፈጣሪዎች ታሪክ ሊቀይሩ እንደሚፈልጉ ይነግራታል። ምንም እንኳን መርማሪው በሞት አፋፍ ቢሆንም አናን ወሳኝ የሆነውን ቀን ህዳር 9 ይጠቁማታል። ግን በየትኛው አመት ማለቱ ነው?

    Mission Berlin 07 – የማይታወቀው ጠላት

    Play Episode Listen Later Feb 18, 2010 5:00


    አና ሞተር ሳይክል ነጂዎቹን ወደ ቫሪቴ ቲያትር ቤት ሄዳ ታመልጣለች። እዛም ሀይድሩንንና መርማሪ ኦጉርን ታገኛለች። እሱም RATAVA እያሳደዷት እንደሆነ ይነግራታል። ግን RATAVA እና ቀይ ለባሿ ሴት ከአና ምንድን ነው የሚፈልጉት? ተጫዋቹ አና ወደ ፓውል ቪንክለር ሱቅ ሄዳ የመጫወቻ ቀፎውን ይዛ እንድትመጣ ያዛታል። ወደእዛ ስትሄድ ሞተር ሳይክል ነጂዎቹን ታመልጣለች። ቲያትር ቤት ሀይድሩን ድራይ ን በድጋሚ ታገኛታለች። መርማሪ ኦጉርም እዛ ብቅ ይልና ሀይድሩን አና የት እንዳለች ይጠይቃል። አና ቲያትር ቤቱ እንደተደበቀች ይጠራጠርና RATAVA እየተከታተሏት ስለሆነ እንድትጠነቀቅ ይላል። ወዲያው ቀይ ለባሿ ሴት ብቅ ትላለች። ከአና ምንድን ነው የምትፈልገው?

    Mission Berlin 06 – ቀይ ለባሿ ሴት

    Play Episode Listen Later Feb 18, 2010 5:00


    አና በ 1961 ጓደኛሞች ነበርን የምትል አንዲት ሴት ታገኛለች። በመጨረሻም አናን አንዲት ቀይ ለባሽ ሴት እንደምትከታተላት ዜና ይደርሳታል። የማይታወቁ ሰዎች አናን በየቦታው ይጠብቋታል። አንዷ ሀይድሩን ድራይ ነች። ከአና ጋር በ1961 ጓደኛ ነበርኩ የምትል። እሷም አናን ለመርዳት ትፈልጋለች። አንዲት ቀይ ለባሿ ሴት አናን እየተከታተለች እንደሆነም ታስጠነቅቃታለች። ለመሆኑ ሀይድሩን ድራይ እንዴት ይሄን ልታቅ ቻለች?

    Mission Berlin 05 – አንተዋወቅም?

    Play Episode Listen Later Feb 18, 2010 5:00


    አና የመጫወቻ ቀፎውን ለማስጠገን ሰዐት ሰሪ ጋር ትመጣለች። ለፓውል ቪንክለር ግን ነገሩ ከጥገና ትዛዝ በላይ ነው። ፓውል ቪንክለር የመጫወቻ ቀፎውን ሲከፍት ውስጡ አንድ ወረቀት ላይ የቁጥር ቁልፍ 19610813 ያገኛል። ምን ማለት ነው? ፓውል ቪንክለር ስለ ምንድን ነው የሚያወራው? አና የመጫወቻ ቀፎውን ልጠግንልህ ትላለች። እሱ ደግሞ ከዚህ በፊት እንደሚተዋወቁ ይገምታል። በመካከልም አና ጨዋታውን መዝግባ ታስቀምጣለች። ከአሁን በኋላ 90 ደቂቃዎችና ሁለት ህይወት አሏት። ሙዚቃውን ተከትላለች ግን "In der Teilung liegt die Lösung" ምን ማለት ነው?

    Mission Berlin 04 – ማስጠንቀቂያዎች

    Play Episode Listen Later Feb 18, 2010 5:00


    አና የካንት መንገድ ላይ አንድ የተዘጋ የሰዐት መሸጫ ታገኛለች። የሱቁ ባለቤት አንድ ካፍቴሪያ እንደተቀመጠ ትሰማለች። ሁለቱም ሳይተዋወቁ አይቀሩም። አና 100 ደቂቃዎች ብቻ ነው ያሏት። ጊዜው ይበቃት ይሆን? አና ሊዮ ቪንክለር በህይወት እንዳለ ትሰማለች። አንድ የፊልሙ ውስጥ የሚሰማውን ሙዚቃ የሚጫወተው ተጫዋች የሱቁ ባለቤት የ ሊዮ ቪንክለር ልጅ ፓውል እንደሆነ ይነግራታል። በቅርብ በሚገኘው ካፍቴሪያ በየቀኑ ቸኮላት ይጠጣል። አናም ወደዚያ ትሄድና ቡና ታዛለች። ካፍቴሪያ የተቀመጠ አንድ የብር ቀለም ያለው ቫይሊን ያነገተ ሰውዬ ሳቅ ይልላታል። መርማሪ ኦጉር ብቅ ይልና አናን ተልዕኮዋ አደገኛ እንደሆነ ይነግራታል። የ RATAVA ማህበር ጨምሮ። አና በጉጉት የብር ቀለም ያለው ቫይሊን ያነገተውን ትልቅ ሰውዬ ትከታተላለች።

    Mission Berlin 03 – ወደ ካንት መንገድ አቅጣጫ

    Play Episode Listen Later Feb 18, 2010 5:00


    አና ወደ ካንት መንገድ አቅጣጫ ታመራለች። መንገድ መጠየቅ ስላለባት ሰአቷ ይባክናል። ጥቁር ኮፍያ ያደረጉ ሞተር ሳልክል ነጂዎች ይደርሱባትና ይተኩሳሉ። ሞተር ሳልክለኞቹ አናን ፋታ አይሰጧትም። በተልዕኮዋ ላይ በተጨማሪም ይረፍድባታል። ተሽከርካሪ ጎማ ያለው ጫማ የሚሄዱትን ልጆች መንገድ ስትጠይቅ ሞተር ሳልክለኞቹ ተኩሰው ይገድሏታል። ጨዋታው በድጋሚ ከተጀመረ በኋላ በመጨረሻ ካንት መንገድ ላይ ትደርሳለች። ግን እዚያ የምትፈልገውን ታገኝ ይሆን?

    Mission Berlin 02 – በማምለጥ ላይ

    Play Episode Listen Later Feb 18, 2010 5:00


    አና የመርማሪውን ጥያቄ እየመለሰች ሳለ የሞተር ሳይክል ድምፅና ተኩስ ይከፈታል። አና ትጠፋለች።የመጫወቻ ቀፎ ላይ አንድ አድራሻ ታገኛለች። ይኼ እሷን ይረዳት ይሆን? አና ከአባራሪዎቿ ወደ አንድ ሙዜም ማምለጫ አጋጣሚ ታገኛለች። ፓሊሶች ወይም ጥቁር ኮፊያ ያደረጉ ታጣቂ ሞተር ሳይክል ነጂዎች እንዳያገኝዋት ስለፈራች የወንዶች መፀዳጫ ቤት ትደበቃለች።

    Mission Berlin 01 – ተንኮል የተሞላነት ቅስቀሳ

    Play Episode Listen Later Feb 18, 2010 5:00


    የአና ተልኮ ጀረመንን ከአደጋ መጠበቅ ነው። እሷም እንቆቅልሹን መፍታትና እራሷን ሞተር ሳይክል ከሚነዱት ወንዶች መጠበቅ አለባት።ለዚህም 130 ደቂቃዎች አሏት። ግን የመጀመሪያዋ ምንጭ የታለ? አና በክፍል 14 የአንድ የጀርመን ሆቴል ከእንቅልፏ ትነቃለች። አንድ የወንጀል ተመራማሪ ወደ ክፍሏ እያመራ ነው። መርማሪ ኦጉር እራሱን ያስተዋውቅና የክፍል ቁጥር 40 አንድ የሆቴል እንግዳ መገደሉን ይገልፃል። የመታጠቢያ ቤቷ መስታወት ላይም: "In der Teilung liegt die Lösung; folge der Musik". የሚል መልዕክት ተፅፎ ያገኛል። አና መርማሪውን ወደ ሆቴሉ አዳራሽ ለጥያቄና መልስ ትከተለዋለች። ግን አና እክፍሏ ያገኘችው አሮጌ የመጫወቻ ቀፎና ይሄ ግራ የሚያጋባ መልዕክት ምንድን ነው?

    Claim Mission Europe – Mission Berlin | ጀርመንኛ መማር | Deutsche Welle

    In order to claim this podcast we'll send an email to with a verification link. Simply click the link and you will be able to edit tags, request a refresh, and other features to take control of your podcast page!

    Claim Cancel