ፓውላና ፊሊፕ ግልጽ ያልሆኑ ጉዳዮችን ይመረምራሉ። ጋዜጠኞቹ በመላው ጀርመን በሚያደርጉት ጉዞ በማጀብ የጀርመንኛ ቋንቋን ይማሩ! ይኸው የትምህርት ክፍል በተለይ አድምጦ የመረዳት ችሎታን ያዳብራል።
የሚያሳዝን ዜና ፦ ባልደረባ አይሀን ወደ ቱርክ ስለሚሄድ ይሰናበታል። ምንም እንኳን የተቀሩት ባልደረቦች ለስንብቱ ስጦታ ቢያዘጋጁም ተደስተው ማክበር ግን አልቻሉም። ፓውላ ጠዋት ወደ ቢሮ እንደመጣች ወዲያው ፓርቲ ማዘጋጀት አለባት። የፓርቲው ምክንያት ግን አላስደሰታትም። አይሀን የ Radio D ዝግጅት ክፍልን ለቆ ወደ ቱርክ አባቱን ለመርዳት ይሄዳል። በስንብቱ ላይም አጭር ንግግርና ጓደኛውን ኡላሊያ የሚያስታውስበት ስጦታ ለአይሀን ይሰጡታል። ለበዐሉ ስንብት ሲሉ ፕሮፌሰሩ በዚህ ምዕራፍ ስለ ሰዋሰው አይመለከቱም። ሆኖም የተወሰነ ነገሮች እንዴት ዋና ቃላቶች እንደሚዋኀዱ ከማለት ወደ ኋላ አይሉም።
ጋዜጠኞቹ "getürkt" የሚለውን ቃል ትርጉም እያፈላለጉ ነው። በተጨማሪም አስገራሚ የሆነ ወደብ ይጎበኛሉ። እዛም እያንዳንዱ መርከብ በተለየ ሁኔታ ሰላምታ ይሰጠዋል። ቪልኮም ሆፍት በተባለው ወደብ እያንዳንዱ መርከብ በክፍለ ሀገሩ ብሔራዊ መዝሙር ሰላምታ ይሰጠዋል። የክፍለ ሀገራቸውን ባንዲራ እያውለበለቡ ይሄዳሉ። በአንድ የማድመጥ ትምህርት ላይ ፊሊፕና ፓውላ የዚህን የስራ ዘርፍ በትክክል ይመለከታሉ። "getürkt" የሚለው ቃል ትርጉምም ከዚህ ስራ ጋር ይገነኛል። የዝግጅት ክፍል ደግሞ አይሀን የረፍት ጊዜውን ስለ ጉጉቶች መፅሀፍ በማንበብ ያሳልፋል። ኡሌሊያ ማንበብ ስለማትችል አይሀን ያነብላታል። ይህም ምዕራፍ የተሳቢ ግሶችን ይመለከታል። አንድ ግስስ እንዴት በተሳቢው አማካይነት ይቀየራል?
ጉጉት ኡላሊያ ጋዜጠኞቹን ወደ ትክክለኛው መስመር ትመራቸዋለች። እነሱም የሀንቡርግ ጋዜጣ አዘጋጆች እጅ ሳይኖርበት እንደማይቀር ይደርሱበታል። ፊሊፕ የሚያደርገውም አስተያየት ፓውላ ትደነግጣለች። የሀንቡርግ ጋዜጣ አዘጋጆች አውቀው ባህር ዳር ታየ የተባለውን የአሳ ነባሪ ታሪክ ፈጥረው እንደፃፉ ፓውላ ፣ ፊሊፕና ኡላሊያ ይደርሱበታል። ይህንንም ያደረጉት የአንባቢያቸውን ቁጥር ለመጨመር ሲሉ ነው። በኋላም ፊሊፕና ፓውላ በሆነ በአንድ ቃል አጠቃቀም ይጣላሉ። ፊሊፕም ፓውላ እንድትረጋጋ ሲል የወደቡ እንኳን ደህና መጡ መቀበያ ጋር ይጋብዛታል። ፊሊፕ ለሚለው ነገር ተጠንቅቆ ቢሆን ኖሮ ፓውላን ባላስቆጣት ነበር። በተረፈ የሚነጠሉ ግሶችን እናያለን። አንዳንድ የግስ ተሳቢዎች የግሱን ትርጉም የበለጠ ያብራራሉ። አልፎ አልፎም ግሱን ከተሳቢው ነጥሎ በቅድመ ቃል መልክ እንዴት መጠቀም እንደሚቻል ምዕራፉ ይመለከታል።
ፓውላና ፊሊፕ አሳ ነባሪ የተባለውን ወሬ ይደርሱበትና የታሪኩን ውሸት ይፈታሉ። ያልተፈታው ነገር ግን ለምን ይህ እንደተደረገ ነው። ወዲያው ሳይጠብቁ ከጉጉት ኡላሊያ እርዳታ ያገኛሉ። የተሰወረውን የባህር ተንሳፋፊ ፓውላና ፊሊፕ እየፈለጉ ሳለ የባህር ውስጥ ጠላቂው ከተባለው አሳ ነባሪ ጋር ሊገናኝ እንደሚችል ይገምታሉ። የባህር ውስጥ ጠላቂው ጀርባው ላይ የአሳ ነባሪ ክንፍ አድርጎ መላውን የሀንቡርግ ከተማ ለፍርሀትና ለድንጋጤ ጥሏል። ግን ለምን ይህን ያደርጋል? በሀንቡርግ ከተማ በመሀል ብቅ ያለችው ኡላሊያ ነገሩን ልታብራራ ትችላለች። እሷም አዲስ ግኝት አድርጋለች። ኡላሊያ አሁን በምታደርገው ጉብኝት የሀላፊ ጊዜያትን የአጠቃቀም ዘዴ ( Vergangenheitsform ) መመልከት ይቻላል። በተጨማሪ የበለጠ ትኩረት የሚሰጣቸው የቅርብ ሀላፊ ጊዜ አጠቃቀምን ነው።
ፊሊፕና ፓውላ ስለ አካባቢው አንድ ፍንጭ ለማግኘት ጉዞ ይጀምራል። እነሱም አዳዲስ የሚገርሙ ግኝቶች ያደርጋሉ፦ ሰርፈረኛ የሌለበት የሰርፍ ጣውላ እና ግራ የሚያጋባ የጋዜጣ ፁሁፍ ትኩረታቸውን ያጠናክረዋል። ከስፍራው ትንሽ ራቅ ብሎ ሁለት ጋዜጠኞች ስለ አስገራሚው አሳ ነባሪ ያፈላልጋሉ። አንድ የባህር ተንሳፋፊ የሌለበት የሰርፍ ጣውላ ክፉ ነገር ሳይከሰት እንዳልቀረ ያመለክታል። በኋላም የሀምቡርግ ጋዜጣ ላይ የተባለውን አሳ ነባሪና የፊሊፕና የላውራን ፎቶ ያገኛሉ። ሁለቱም በፍርሀት ይመለከቱ ነበር። ግን ይሄ ሁላ እንዴት አንድ ላይ ትርጉም ሊሰጥ ይችላል? ቢያንስ ሰዋሰውን ስንመለከት ትርጉም የሚሰጡ ነገሮች አሉ። ይህ ምዕራፍ የበለጠ ትኩረት የሚሰጠው "sie" እና "er" ለሚሉት ተወላጠ ስሞች ነው። ከዚህ በፊት በነበረው ክፍል የተመለከትናቸውን አርቲክሎች ከዋናው ቃል ጋር መዛመድ ያስፈልጋል።
በ Radio D ዝግጅት ክፍል ያለው አስቀያሚ ያየር ጠባይ ነው። ወደ ባህር አካባቢ የሚያስልክ የምርምር ትዕዛዝ በአሁን ሰዐት አስደሳች ነው። ፊሊፕና ፓውላ ወደ ሀንቡርግ ለዚሁ ጉዳይ ይሰደዳሉ። እዛም አንድ አሳ ነባሪ የወደቡ አፋፍ ላይ ሳይንጎራደድ አይቀርም። ፓውላ ፣ ፊሊፕና አይሀን ቀላል ጊዜ አይደለም የሚጠብቃቸው። በቢሮ ውስጥ ያለው ሙቀት የሚቻል አይደለም። ክፍሉ ደግሞ ማቀዝቀዛ እንኳን የለም። የፓውላ ወደ ባህር ወይም ውቅያኖስ ለመሄድ መመኘት ኮምፑን በትንሹም ቢሆን ያረካል። ጋዜጠኞቹ አሳ ነባሪ ወደታየበት የሀንቡርግ ወደብ መጓዝ አለባቸው። አሳ ነባሪ የተባለውን ያዩት የሰዎች ብዛት ሲታይ ሁለቱ ጋዜጠኞች ምንም ሊያመልጣቸው አይችልም። ይህ ለፕሮፌሰሩም ከባድ ነው። የ ተባዕት ፆታ አርቲክል የቀጥተኛ ተሳቢ መምንጠቀምበት ጊዜ፤ የቃሉ ማብቂያ እንዴት እንደሆነ ለማብራራት ፕሮፌሰሩ ብዙ መጣር አለበት። "kein" የሚለው አፍራሽ ቃል ከዋናው ቃል ጋር መዋኸድ አለበት።
ፊሊፕና ፓውላ አድማጮቹ ያላቸውን አስተያየት ይጠይቃሉ። የ መርሀ ግብሩ ጭብጥ ውሸት ሀጢያት ሊሆን ይችላልን? "Kann denn Lüge Sünde sein?" ይሰኛል። እዚህ ጋር አድማጮች ስለ ውሸተኞቹ ክብ የበቆሎ ቆረኖች የሚያስቡትን መናገርና በተጨማሪም የገበሬዋቹን እርምጃ መገመት ይችላሉ። ውሸት ሀጢያት ሊሆን ይችላልን? "Kann denn Lüge Sünde sein?" ፊሊፕና ፓውላ ዛሬ አድማጮችን የሚጠይቁት ጥያቄ ነው። መነሻው ሁለቱ ጋዜጠኞች የዘገቡባቸው ክብ የበቆሎ ቆረኖች ናቸው። ይህ የገበሬዎቹ ማታለል ፤ ጎጂ አልያስ የገራገር ጎብኝዎቹ የግል ጥፋት ነው? ግን የአድማጮች መልስ ግልፅ ነው። የጋዜጠኞቹን ጥያቄ አዎ አልያም አይደለም በሚል ከሚመልሱት አድማጮች ባሻገር ፕሮፌሰሩ ሶስት አማራጭ መልሶች ያሉትን መጠይቅ ያዘጋጃል። በጀርመንኛ ቋንቋ ከአንስታይ (Femininum) እና ተባዕት ፆታ (Maskulinum) ባሻገር ሶስተኛ ከሁለቱም ያልሆነ ፆታ Neutrum አለ። እነዚህም "der", "die" እና "das" በተሰኙ አርቲክሎች ይብራራሉ።
ምንም እንኳን ክብ የበቆሎ ቆረኖቹን ገበሬዎቹ ቢሆኑም ያደረጉት ኡላሊያ ግን ኡፎዎች ይኖራሉ ብላ ታምናለች። ፓውላና ፊሊፕ የሰፈሩን ነዋሪዎች ሲጠይቁ ስለ ክቡ የበቆሎ ቆረኖች ውሸት ይሰሙና ወደ መጠጥ ቤት ያመራሉ።ፓውላና ፊሊፕ የክቡን የበቆሎ ቆረኖች ውሸት ያረጋግጣሉ። ግን ኡፎዎች ምናልባት ይኑሩ አይኑሩ እርግጠኛ አይደሉም። ለመሆኑ UFO ሲተነተን ምንድን ነው? ስለዚያ ኡላሊያ ልታብራራ ትችላለች። ይህ ብቻ ሳይሆን ከኡፎዎቹ አንድ ሳታይ እንደማትቀር እርግጠኛ ነች። በመጨረሻም ሁለቱ ጋዜጠኖች በመንደሩ መጠጥ ቤት የሚገኙትን እንግዶች ስለ ክብ የበቆሎ ቆረኖቹ ውሸት የሚያስቡትን ይጠይቃሉ። ይህ የመጠጥ ቤቱ እንግዶች ትውስታ ሀላፊ ጊዜን (Präteritum) ለመጠቀም ጥሩ አጋጣሚ ነው። ሀላፊ ጊዜው መደበኛ ያልሆነው የመሆን ግስን unregelmäßige Verb "sein" ያካትታል በተጨማሪም "können" የሚለው ግስ በድጋሚ ይብራራል። ትኩረት መሰጠት የሚገባው ሌላው እንዴት የአንድ ግስ መሰረት የአነባቢ ፊደሎቹን እንደሚለውጥ ነው።
ፓውላና ፊሊፕ የክቡን ሚስጥር ለማግኘት በሙከራ ላይ ናቸው። እርሻውንም ይመለከታሉ። ግን በምድር ላይ የማይኖሩ ፍጥረታት ይህንን እንደሰሩ የሚያሳይ ምንም ነገር አያገኙም። የእርሻው ባሌቤት ቀን ቀን ጎብኝዎች ፎቶ ለሚያነሱበት አምስት ዮሮ ሲቀበል ፓውላና ፊሊፕ ሌሊት ሜዳ ላይ ተደብቀው ተኝተዋል። ኡፎዎችን እየጠበቁ ነው። በነሱ ፋንታ ሁለት መሳሪያ የያዙ ወንዶች ይመጣሉ። እነሱ ናቸው ሜዳው ላይ ጎብኝዎችን ለመሳብ ክቦቹን የሳሉት? በመጨረሻም አንድ ኡፎ ብቅ ብሎ ግርግር የፈጠረ ይመስላል። የበቆሎ ሜዳ ላይ ከተከሰተው የማይተናነስ "machen", ወይም ማድረግ የሚለው ብዙ አይነት ገጽ ያለው ግስ ነው። ፕሮፌሰሩ በተለያዩ ምሳሌዎች አማካይነት የቃሉን አጠቃቀም ያሳያሉ።
ታምራዊ ክብ የሆኑ የበቆሎ እርሻዎች ላይ ያሉ ቆረኖች ፓውላንና ፊሊፕን ስቧቸዋል። ይሄ የ ኡፎዎች ማረፊያ ነው ወይስ እዚህ አንዱ በጎብኝዎች መነገድ ፈልጎ ነው?አይሀን ወደ ዝግጅት ክፍል ሲመለስ ፓውላና ፊሊፕ ለአንድ ዝግጅት ወጣ ብለዋል። በአንድ የበቆሎ እርሻ ላይ እንቆቅልሽ የሆኑ ክብ ቆረኖች አሉ። ማን እንዳጨዳቸው የማይታወቁ ። ክል እንደ ሁለቱ ጋዜጠኞች ሌሎች ጎብኝዎችንም እነዚህ ምስሎች ስቧቸዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች ወዲያው እንዴት በዚህ አጋጣሚ ገንዘብ እንደሚያተርፉ ገብቷቸዋል። ብዙ ግርግር በበዛበት የተለያየ ፍላጎት ያላቸው ብዙ ሰዎች ይገናኛሉ። ጎብኝዎቹ ለሚያጓጓቸው ነገር መልስ ይሻሉ። ጋዜጠኞቹ ደግሞ እንቆቅልሹን መፍታት። ገበሬዎቹ ደግሞ ገንዘብ ማግኘት። በተጨማሪም በትክክል "wollen" ወይም መፈለግ የሚለውን ሞዳል ግስ እንመለከታለን።
የግሪክ ታምር ላይ ያለው የሚያሳዝነው ጀግና ኢካሩስ ሁለቱን ጋዜጠኞች ይስባቸዋል። ግን አድማጮች ኢካሩስ ማን እንደሆነ ለመሆኑ ያውቃሉ?ፓውላና ፊሊፕ ስለሱ ማንነትና ታሪክ ያብራራሉ። እንደ ኢካሩስ የለበሰ አንድ ትንሽ ልጅ ፓውላንና ፊሊፕን ወደ አንድ ሀሳብ ይከታቸዋል። በአንድ የማድመጥ ምሳሌ ላይ የግሪክን አባባሎች ይመለከታሉ። እዛ ላይም አባቱ ዴዳሉስ ተው ሲለው ከበረራ የወደቀውን ህፃን ኢካሩስን ይመለከታል። እሱም ፀሀይ ጋር ለመቅረብ ያደረገውን ጥረት የክንፎቹ ሰም እስከሚቀልጥ ድረስ አላቋረጠም። "Flieg nicht zu hoch, flieg nicht zu tief" ወይም ከፍ ብለህ አትብረር ዝቅ ብለህም አትብረር ይላል ዴዳሉስ ልጁን ኢካሩስን። እዚህ የምንመለከተው ትዕዛዛዊ አነጋገር (Imperativ )ልመና ፣ ትዕዛዝና ማስጠንቀቂያ ሊሆን ይችላል። ኢካሩስ የአባቱን ምክር እንደ ትዕዛዝ አይቶ ቢሆን ኖሮ ምናልባት ባልወደቀ ነበር።
ፓውላና ፊሊፕ ከአደባባይ በድጋሚ ስለ ካርኔቫል ስርዐት ይዘግባሉ። በዛ ላይ የተለያዩ የካርኔቫል ልብሶችንና የተለያዩ የጀርመንኛ አነጋገሮችን ይተዋወቃሉ። ወደ ቢሮ ፓውላ ስትመለስ አይሀን ላይ ብድሯን ትከፍላለች። በኋላም በሚገርም ሁኔታ ስለ ካርኔቫል አለባበስ ታነሳለች። ፓውላና ፊሊፕ ከአደባባይ ስለ ትክክለኛው የካርኔቫል ልብሶች ይዘግባሉ። የሞዛርት ኦፔራ "Die Zauberflöte" ወይም የአስማት ዋሽንት የተሰኘው የሙዚቃ ቲያትር ላይ ያለ አንድ ምስል(ፓፓጌኖን) እና የግሪክ ታዋቂ ጀግና የሆነውን ኢካሩስን ያያሉ። በካርኔቫል ወቅት ፓውላና ፊሊፕ ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ ሰዎችን ይተዋወቃሉ። እናም የተለያየ የጀርመንኛ አነጋገር ዘዬ ይሰማሉ። ይህ ምዕራፍም የሚመለከተው ይሆናል።
ፊሊፕ ከእሽቫርስቫልድ እንደተጠበቀው ይዘግባል። እሱም ካርኔቫል ከሚያከብሩ ሰዎች ጋር በደስታ ይቀላቀላል። የሱ ባልደረባ የሆነችው ፓውላ ግን የበዐሉን ስርዐት አልወደደችውም። ፊሊፕ የካርኔቫል አከባበር አስደስቶታል። ጫጫታና ግርግሩ ግን ፓውላን አበሳጭቷታል። እሷ ፊሊፕን እየፈለገች ብቻ ሳይሆን የሱን የተሰረቀም መኪና መፈለግ አለባት። በዚህ ላይ ፊታቸውን ቀለም የተቀቡና የሸፈኑ ሰዎች ፍለጋዋን ከባድ አድርገውባታል። ይህ አልበቃ ብሎ አይሀን ደግሞ እስቀያሚ የሆነ ቀልድ ፓውላ ላይ ይቀልዳል። ልክ እንደ ካርኔቫል ልብሶች የሚለያይ "sein" የሚለው ግስ አጠቃተም ነው። ይህ ምዕራፍ የተለያዩ የግስ ማሟያዎችን ይመለከታል።
የ Radio D ዝግጅት ክፍል ሰራተኞች ስለ ካርኔቫል ያላቸው አመለካከት የተለየ ነው። ኮምፑ እንዲያፈላልግ የተሰጠው ትዕዛዝ ሁለቱን ጋዜጠኞች የካርኔቫልን በዐል ወደሚያደንቁት እሽቫርስቫልድ ቦታ ያመራቸዋል። ግን ይኼ ለሁሉም ተካፋዮች አስደሳች አይሆንም። ካርኔቫል በአንዳንድ የጀርመን አካባቢዎች በደንብ ይከበራል። በባህላዊው ሮዝን ሞንታግ ተብሎ በሚጠራው ሰኞ ቀን ቢሮ ውስጥ በበዐሉ የተነሳ ብዙ አለመግባባት ተፈጠረ። ፓውላ ፊሊፕ የጠንቋይ ልብስ መልበሱን አልተቀበለችውም። ልብሱ የመጨረሻ አስቀያሚ ነው ትላለች። ፊሊፕ ጥናት ለማድረግ ወደ እሽቫርስቫልድ ወደሚባለው ቦታ ስለሚሄድ ደስተኛ ነው። እዛም የጠንቋይ ልብስ የለበሱ የካርኔቫል መኪና ላይ ቆመዋል። ሁለቱ ጋዜጠኞች በቀጥታ የሚተላለፍ ዝግጅት ማድረግ ይፈልጋሉ። ሆኖም ይህ አሁን ሊሆን አይችልም። ፊሊፕ የጠብቋይ ልብስ በለበሱት ሰዎች ከመኪና ተጓትቶ ይጠለፋል። እንደ ካርኔቫል ቀናቶች መላ የሌለው የጀርመንኛ የአረፍተ ነገር አቀማመጥ ነው። ግን ባለቤትና ግሶችን ስንመለከት ነገሮች ግልፅ ይሆናሉ።
ግልፅ ያልሆነ ነገር ካለ መጠየቅ ጥሩ ነው። አንድ ፕሮፌሰር ከዚህ በፊት በነበሩት ምዕራፎች ላይ ጥያቄ ካለ መልስ ይሰጣሉ። ይኼ የነበሩትን ፍሬ ነገሮችን ለመከለስ ጥሩ አጋጣሚ ነው። አድማጮች ይጠይቃሉ፤ ፕሮፌሰሩ ይመልሳሉ። እሳቸውም ለሁሉም ጥያቄዎች በዝርዝር ይመልሳሉ። ይኼ ለአድማጮች ፍሬ ነገሮችን ለመከለስና የቋንቋ ችሎታቸውን የበለጠ ለማዳበር ጥሩ አጋጣሚ ነው። ሁሌ ለመጠየቅ ይፈልጉ የነበሩ ጥያቄዎች ካሉ መልስ ያገኛሉ። የአድማጮች ጥያቄዎች፦ በየትኛው አጋጣሚ የትኛውን አጠራር መጠቀም ይቻላል? ማንን "du" አንተ/ቺ ወይም "Sie" እርስዖ ማለት እችላለው? እራሴን እንዴት ማስተዋወቅ እችላለሁ? መቼ በስሞች (Vornamen) መቼ ደግሞ በአባት ስሞች (Nachnamen) መጥራት እችላለሁ? "denn", "doch" እና "eigentlich" የሚሉት የአረፍተ ነገር ማሟዮች የትኛው ትርጉም አሏቸው? "nicht" እና "nichts" የሚሉት ቃላቶችስ ልዩነት ምንድን ነው?
ለመሆኑ ኡላሊያ የሚለው ስም ከየት ነው የመጣው? ኮምፑ፣ አይሀን እና ዮሴፊን ትርጉሙን ያጠያይቁና ብዙ መልሶች ያገኛሉ። ስለ ጉጉቷ በዝግጅቱ ክፍል መገኘት የሰማ አንድ የስፓኝ ባልደረባ ደግሞ መልስ ለመስጠት ይተባበራል። ጉጉት ኡላሊያ የስሟን ትርጉም ለማወቅ ጓጉታለች። የ Radio D ዝግጅት ክፍል ትርጉሙን ሲያፈላልግ ቃሉ ከግሪክ እንደመጣ ይደርስበታል። የስፓኝ ዝግጅት ክፍል ባልደረባ የሆነው ካርሎስ እሱም በዚህ ጉዳይ አንዳንድ ጥሩ መረጃዎች አሉት። እሱም አንድ እንደዚህ አይነት ስም ያላት ቅዱስ ያውቃል። በዝግጅቱ ክፍል አሁንም መልስ ያላገኙ ብዙ ጥያቄዎች አሉ። በዚህ አጋጣሚ የጥያቄ አረፍተ ነገሮችን የመጠየቂያ ቃላቶች ያሏቸውን ወይም የሌላቸውን መመልከት ጠቃሚ ነው። በተጨማሪም ቅያቄ ሲጠየቅ የድምፅ አወጣጡን ይመልከቱ።
ፊሊፕ የሙዚቃ አተራረክ ላይ ንጉስ ሉድቪግን ሆኖ የሚጫወተውን ሰው ያገኝና ቃለመጠይቅ እንዲሰጠው ይለምነዋል። ወዲያው ድምፁን የሚያውቀው ይመስለዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ዝግጅት ክፍል ያልተጠበቀ እንግዳ ይመጣል። ፊሊፕ ያለ ፓውላ እርዳታ በኖይሽቫንእሽታይን ቤተ መንግስት እያለ የሞተው ንጉስ ሉድቪግ ነኝ ያለው ማን ሊሆን እንደሚችል መልስ ያገኛል። እሱም የንጉስ ሉድቪግ ሙዚቃዊ አተራረክ ተዋንያን ነው። ፊሊፕ ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም ተዋንያኑን ለቃለ መጠይቅ ፍቃደኛ መሆኑን ይጠይቀዋል። ፊሊፕ ወደ Radio D ሲመለስ አንድ የምትናገር ጉጉት በዝግጅቱ ክፍል ያገኛል። ይኼ ምዕራፍ ለፊሊፕ ብዙ አስደናቂ ነገሮችን ይዞ ቀርቧል። እኔ አላምንም "Das glaube ich nicht" እና አላውቅም "Das weiß ich nicht" በተደጋጋሚ ፊሊፕ ይላል። "nicht" የሚለውን አፍራሽ መጠቀም ይቻላል።
ፊሊፕም የማይታወቀው ሰውዬ ማን ሊሆን እንደሚችል ለማወቅ መንገድ ያገኛል። ጋዜጣ ላይ አንድ ማስታወቂያ ስለ ንጉስ ሉድቪግ ሙዚቃዊ አተራረክ ያያል። ወደእዛ ሲጓዝ ከብዙ አገር የመጡ የአገር ጎብኝዎችን ይጠይቃል። ፓውላ በርሊን ቢሮ ተቀምጣ ሳለ ፊሊፕ ወደ ሙኒክ እየተጓዘ ነው። እሱም የስራ ባልደረባው ስላገኘችው ውጤት ገና አላወቀም። ግን ፓውላም እንቆቅልሹን ለመፍታት በትክክለኛው መንገድ ላይ ነች። አንድ የሙዚቃዊ አተራረክ ማስታወቂያ ስለ ንጉስ ሉድቪግ ያለውን ፍላጎት እንዲጨምር ያደርገዋል። አውቶቢስ ውስጥ ከብዙ አገር የመጡ የአገር ጎብኝዎችን ከሙዚቃው ትረካ ምን እንደሚጠብቁ ይጠይቃቸቃል። ይኼ ምዕራፍ በማዳመጥ የመማር ችሎታን ያዳብራል። በአውቶቢስ ውስጥ ከተለያዩ ቋንቋዎች ጀርመንኛን መለየት ይመለከታል። በተጨማሪም ከግስ በኋላ የሚገባውን "nichts" የሚለውን አፍራሽ ቃል ያጠቃልላል።
ፓውላና ፊሊፕ ቤተ መንግስቱ ውስጥ ንጉስ ሉድቪግ ነኝ የሚለውን ሰውዬ ይጠይቃሉ። ፓውላ ባጋጣሚ አስደናቂ የሆነ ነገር ታገኛለች። የማይታወቀው ሰውዬ ማን ሊሆን እንደሚችል ይገለፅላታል። ሁለቱ ጋዜጠኞች ከሞት ተነስቻለው የሚለውን ንጉስ ሉድቪግ ቃለመጠይቅ ለማድረግ ይችላሉ። ሆኖም የማይታወቀው ሰውዬ እውነተኛ ማንነት አጠራጣሪ ነው። ፓውላ ወደ ቢሮ ስትመለስ አንድ ማስታወቂያ ለእንቆቅልሹ መልስ ሊሆን የሚችል የሆነ ሀሳብ ላይ ይጥላታል። ማስታወቂያው ላይ የሚሰማው ድምፅንም የምታውቀው ይመስላታል። ማንንና ምን እንደሚወዱ ሳይገልፁ ስለ ፍላጎት ለመናገር ይከብዳሉ። ማፍቀር ወይም "lieben" የሚለው ተሳቢ ግስ (Verbergänzung) ማለትም ቅፅል (Akkusativobjekt) ያስፈልገዋል።
ፓውላና ፊሊፕ የባየሩን ስነ-ውበት አድናቂ (ንጉስ ሉድቪግን) ያስተዋውቃሉ። በለሊትና በበረዶ ከእንጨት የተሰሩ ገንዳ መሰል መንሸራተቻዎች ላይ ተቀምጦ በፈረስ መጎተትና ጫጫታ የበዛበት ድግሶች የሉድቪግን ጊዜ ያስታውሳሉ። ሁለቱ ጋዜጠኞች አድማጮችን ወደ 19 ኛው ክፍለ ዘመን ይዘው በመጓዝ የሚደነቀውን ንጉስ ሉድቪግን ያስተዋውቃሉ ፦ ለተፈጥሮ ያለውን ፍቅር፤ ለ ሪቻርድ ቫግነር ሙዚቃዎች የነበረውን አድንቆ፤ ከአክስቱ ልጅ ጋር የነበረውን ልዩ ቅርበት፤የ ታዋቂዋ ንግስት ሲሲ። አዲስ ሉድቪግ የፈጠረው ጠሬቤዛ የመሳሰሉት አድንቆን ይስባሉ። ይኼ ምዕራፍ ስለ ሉድቪግ ፍላጎቶች ያወራል። «ማፍቀር ወይም lieben » የሚለውን ግስ ለመቃኘት ያስችላል። «መምጣት ወይም kommen» የሚለውም ግስ አንድ አይነት ማለቂያ አለው። ይህንንም ግስ ምዕራፉ ይመለከታል።
በኖይሽቫንእሽታይን ቤተ መንግስት ፓውላና ፊሊፕ የሚያስደንቅ ሰው የንጉስ ሉድቪግን ካፓርት ያደረገ ያገኛሉ። ሁለቱም ሁኔታው ከንጉስ ሉድቪግ ሞት ጋር ምን እንደሚያገናኘው ያጠናሉ። የንጉስ ሉድቪግን ካፓርት ያደረገው ሰው ፓውላና ፊሊፕ የሞተው ንጉስ እሱ እንደሆነ ለማሳመን ይሞክራል። ግን ንጉስ ሉድቪግ እንዴት ሞተ? ሁለቱ ጋዜጠኞች በራዲዮ ድራማ ግልፅ ያልሆነውን የ እሽትራንበርገር ሀይቅ ግድያ በተለያዩ መንገድ ያንፀባርቃሉ። ወሳኙ ጥያቄ እንደሚከተለው ነው፦ ተወዳጅ ባልነበረ ገዢ ላይ የተደረገ ግድያ ነበር ወይስ የሚያስደንቅ የራስ ግዲያ? ከማይታወቀው ሰውዬ ጋር የተደረገው ቆይታ የሚያውቁትንና የማያውቁትን ሰው እንዴት ማናገር እንዳለብዎ ያስተምራል። በተጨማሪም « እርስዎ» እና «አንቺ/ተ» የሚሉትን አጠቃቀሞችና « የድርጊት» ግሶችን "sein" ይመለከታል።
ፓውላና አይሀን አዲሱን የስራ ባልደረባ Radio D ውስጥ ይቀበሉታል። ወዲያው ለጋዜጠኞች ስራ ይገኛል። የሞተው የባየር ንጉስ ሉድቪግ በህይወት አለ ይባላል። በቦታው የሚደረገው ምርመር ነገሮችን ግልፅ ማድረግ አለበት። ፊሊፕ የስራ ባልደረባዎቹን ፓውላ፤ አይሀንና የምትገርመዋን ዮሰፊን ( ቢሮ ውስጥ ሁሉም ነገር መልክ እንዲይዝ የምታደርገውን )ይተዋወቃል። የ Radio D ዝግጅት ክፍል እንደተደረሰ ማረፊያ ጊዜ ምንም የለም። የፊሊፕና ፓውላ የመጀመሪያ ትዕዛዝ እየጠበቀ ነው ፦ ገናና የሆነው የባየርኑ ንጉስ ሉድቪግ II በህይወት እንዳለ ወሬ ይሰማል። በ 1986 ዓ ም እ ኤ አ በሚገርም ሁኔታ ህይወቱን አቷል። ሁለቱ ጋዜጠኞች የኖይሽቫንእሽታይን ቤተ መንግስት ሄደው ጥናት ሲያደርጉ የሚገርም ሰው ይተዋወቃሉ። የምያስገርሙ ድርጊቶች ብዙ ጥያቄዎች እንዲነሱ መንስዔ ይሆናሉ። ይህ ምዕራፍ የጥያቄ ቃሎችና መልሶች እንዴት እንደሚሰጡ በደንብ ለመቃኘት አጋጣሚዎች ይሰጣል።
ፊሊፕ የዝግጅት ክፍል እየተጠበቀ ነው። ፓውላና አይሀን (የወደፊት የስራ ባልደረባው) ሰአታቸውን እያቃጠሉ ነው። ፊሊፕም ብቅ ሊል አላቻለም። በስልክ ለመገናኘትም አልተቻለም። ፊሊፕ በአስቀያሚው አየር ምክንያት በጣም ያረፍዳል። ፓውላን በስልክ አግኝቶ ለመንገር ይሞክራል። ግን ሊያገኛት አልቻለም። ፓውላና የስራ ባልደረባዋ አይሀን በመጨረሻም ቢሮውን ለቀው ይሄዳሉ። የፊሊፕ እናት የዝግጅት ክፍሉ ስትደውል ነገሮች የበለጠ ግራ የሚያጋቡ ይሆናሉ። ፊሊፕ አርፍዶ በመምጣቱ ይቅርታ ለመጠየቅ ይሞክራል። አድማጭም የተለያዩ የይቅርታ አሰጣጥ አይነቶች መማር ይችላል።
ፊሊፕ ወደ በርሊን ጉዞ ይጀምራል። ነገሮች ግን እንደጠበቀው ቀላል አይሆኑም። አስቀያሚው አየር እቅዱን ያደናቅፉበታል። በመካከል አዳዲስ ሰዎችን ይተዋወቃል። ፊሊፕ በመኪና ወደ ሙኒክ የአይሮፕላን ማረፊያ ይጓዛል። ቀጥሎም ከዛው ወደ በርሊን መብረር ይፈልጋል። የአየሩ ሁኔታ እንደተነገረው ሀይለኛ ዝናብና መብረቅ ይዞ መቷል። በዚህ ምክንያት ጉዞው ይዘገያል። ይህ በንዲህ እንዳለ የ Radio D ክፍል ሰራተኞች ፊሊፕና እናቱን ጨምሮ አንድ ጊዜ በዚህ ምዕራፍ እራሳቸውን በትክክል ያስተዋውቃሉ። የተለያዩት የሰላምታ አሰጣጥ፣ እንዴት ለጓደኛ ወይም ለአለቃ ሰላምታ እንደሚሰጥ ግልፅ ያደርጋሉ።
ፊሊፕ ፋታ ሊያገኝ አልቻለም። የሚናከሱ ነፍሳቶች ሰላም አልሰጥ ማለታቸው ሳያንስ የጎረቤት ጫጫታ አላስቀምጥ ብሎታል። ያልተጠበቀ ስልክ ደሞ ከበርሊን ይደወልለትና በፍጥነት ወደ Radio D ጉዞ ይጀምራል። ፊሊፕ ወደ ክፍለ ሀገር ሄዶ እንደጠበቀው እንዲዝናና ማንም የተመኘለት ያለ አይመስልም። አንድ ክብ መጋዝና አንድ ጥሩ ዋሽንት መጫወት የማይችል ሰውዬ ብስጭት ያደርጉታል። በዚህ አጋጣሚ በርሊን Radio D ከምትሰራው ፓውላ የመጣው የስልክ ጥሪ በሰአቱ ነበር። ፊሊፕ ሱሪ ባንገት ብሎ እናቱን አስቀይሞ ወደ ዋና ከተማው ይመጣል። እዚህ ጋም በጥቂት ቃላቶች አማካኝነት ምን እንደተከሰተ ለማወቅ ይቻላል። በተለይም አለም አቀፍ የሆኑት ቃላቶችና የድምፅ አወጣጥ፤ ክስተቱን የበለጠ ለመረዳትና የማድመጥ ችሎታን ለማዳበር ይረዳሉ።
ወጣት ፊሊፕ በመኪና ወደ ክፍለ ሀገር ይጓዛል። እናቱን ሀነ ለመጠየቅ በመሄዱ ለመዝናናት ችሏል። ግን ወዲያው ፊሊፕ የክፍለ ሀገር አስቀያሚ ጎኖችን ያያል። ፊሊፕ እናቱን ለመጠየቅ ወደ ክፍለ ሀገር ሄዶ እየተዝናና ሳለ ተፈጥሮ እንዴት ያምራል "Natur pur, wie schön", ይላል። ግን ከከብቶችና ለድመቶች ሌላ እንስሳዎችም ገጠር ውስጥ ይኖራሉ። ግቢ ተቀምጦ ቡና መጠጣት አልቻለም። የሚናከሱ ነፍሳቶች ፊሊፕን ሰላም አልሰጥ ብለውታል። በዛ ላይ ደግሞ አንድ ከባድ የሆነ ችግር ያጋጥመዋል። በጣም ትንሽ ቃላቶች የሚገባው ሁሉ ድርጊቶቹ ሊገባው ይችላል። ከበስተ ኋላ የሚሰሙት ድምፆች ፊሊፕ የት እንዳለ ግልፅ ያደርጋሉ። በተጨማሪም አድማጮች የሰላምታና የስንብት አሰጣጥ ልማራሉ።