Listen to interviews, features and community stories from the SBS Radio Amharic program, including news from Australia and around the world. - የአውስትራሊያና ዓለም አቀፍ ዜናዎችን አካትቶ፤ ቃለ ምልልሶችን፣ ዘገባዎችንና የማኅበረሰብ ታሪኮችን ከኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ ፕሮግራም ያድምጡ።
አውስትራሊያ እና ቻይና የፍራፍሬ ንግድ ስምምነትን ተፈራረሙ
የኢትዮጵያውያን የእድር መረዳጃ ማህበር በቪክቶርያ ባሳለፍነ ሰሞን አጠቃላይ የአባላት ስብሰባ ማድረጉ ይታወሳል ፡፡ የማህበሩ ሊቀመንበር ወ/ሮ ማህሌት ማስረሻ ፤ ወ/ሮ ቅድስት ሰለሞን ጸሀፊ እንዲሁም አቶ ዮናስ ደገፋ ገንዘብ ያዥ ፤ እድሩ ከነበረበት ተነስቶ በአሁን ሰአት ምን ደርጃ ላይ እንዳለ እና እና የወደፊት እቅዶቻቸውን በተመለከተ ሀሳባቸውን አጋርተውናል ፡፡
ከኢትዮጵያ ከሀምሳ አምስት እስከ ሰማኒያ በመቶ የሚሆነው ገንዘብ በህገ ወጥ ንግድ ሳቢያ ከአገር ወስጥ እንደሚወጣ የአፍሪካ ልማት ባንክ አስታወቀ፡፡
ወ/ሮ መሠረት አሰፋ፤ የ Habesha Spices and Events መሥራች፤ መጪውን የኢትዮጵያውያንን አዲስ ዓመት 2018 ቅበላና የኤርትራውያንን ቅዱስ ዮሐንስ በዓላት እንደምን በጋራ ድምቀትን በተላበሰ ሁኔታ ለማክበር መሰናዶ ላይ እንደሚገኙ ይገልጣሉ።
በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ቦርድ ሊቀመንበር አቶ ጋሻው አንለይና በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ቦርድ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ታጠቅ መንጂ፤ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ማኅበር መተዳደሪያ ደንብ አፈፃፀም፣ በቦርድ አስፈላጊነት እና አላስፈላጊነት ላይ ያሉ አተያዮችን አስመልክተው አቋማቸውን ያንፀባርቃሉ።
በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ቦርድ ሊቀመንበር አቶ ጋሻው አንለይና በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ቦርድ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ታጠቅ መንጂ፤ ከማኅበር እስከ ቦርድ ምሥረታ የነበሩ ሂደቶችንና በቦርድና የማኅበሩ የሥራ አስፈፃሚ አባላት መካከል ተከስተው ያሉ የሥራ ግንኙነቶች መሻከርን አንስተው ይናገራሉ። የመፍትሔ ሃሳቦችንም ይቸራሉ።
The representation of Indigenous Australians in media has historically been shaped by stereotypes and exclusion, but this is gradually changing. Indigenous platforms like National Indigenous Television (NITV) and social media are breaking barriers, empowering First Nations voices, and fostering a more inclusive understanding of Australia's diverse cultural identity. Learning about these changes offers valuable insight into the country's true history, its ongoing journey toward equity, and the rich cultures that form the foundation of modern Australia. Understanding Indigenous perspectives is also an important step toward respectful connection and shared belonging. - የአውስትራሊያ ነባር ዜጎች የሚዲያ ውክልና ታሪካዊ ተሞክሮው በጅምላ ፍረጃና መገለል የተቀነበበ ነው፤ ምንም እንኳ በዘገምታ በመለወጥ ላይ ያለም ቢሆን። እንደ ብሔራዊ የነባር ዜጎች ቴሌቪዥን (NITV) እና ማኅበራዊ ሚዲያ ያሉ መድረኮች ጋሬጣዎችን በጎን አልፈው፤ የነባር ዜጎችን ድምፆች እያሰሙና የአውስትራሊያን ዝንቅ ባሕላዊ ማንነት በላቀ አካታችነት እየታደጉ ይገኛሉ። ስለ እኒህ ለውጦች፤ የሀገሪቱን እውነተኛ ታሪክ ፣ ያልተቋረጠ የፍትሕ ፍለጋ ጉዞና የበለፀገው ባሕል እንደምን ለዘመናይቱ አውስትራሊያ መሠረት እንደሆነ ጥልቅ ግንዛቤን ለማስጨበጥ ጋባዥ ነው። የነባር ዜጎችን አተያዮች መረዳት ከበሬታን ወደ ተላበሰና የጋራ ጉድኝት ወደ አቆራኘ ጠቃሚ እርምጃ አምሪ ነው።
Learn how to describe people who inspire you. - Learn how to describe people who inspire you.
ቻይና የኢትዮጵያ አኩሪ አተር ምርቶች ወደ ሀገሯ እንዲገቡ ፈቃድ ሰጠች
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ስጋትን፣ ግጭትን፣ ጥርጣሬንና አለመተማመንን የሚፈጥር ድርጊት ፈፅመዋል ያላቸውን የፖለቲካ ፓርቲዎች ከምዝገባ እንዲሰርዝ ስልጣን የሚሰጥ አዲስ የአዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ ለፓርላማ ቀረበ
አቶ ዳንኤል አለማር፤ የጎጆ ካፌና ሬስቶራንት ባለቤት የቡናና ምግብ አቅርቦታቸው ለሽልማት የመጨረሻ ማጣሪያ ከቀረቡት 15 የሜልበር ምርጥ ካፌዎች አንዱ ለመሆን በመብቃቱ "የሬስቶራንቴ ስም 'ጎጆ የኢትዮጵያ ካፌ እና ሬስቶራንት'፤ ሀገርን ተሸክሞ ያለ ትልቅ ስም ያለው ነው። ሀገሬን በማስጠራቴ ትልቅ ኩራት ተሰምቶኛል" ሲሉ፤ እህታቸውና ሥራ አስኪያጅ መሠረት አለማር ፤ ሕልማቸው በዕጩነት ከ15 ምርጥ የሜልበርን ካፌና ሬስቶራንት ውስጥ አንዱ ለመሆን በመብቃት እንደማይገታ ይናገራሉ።
ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው፤ በቪክቶሪያ የኢትዮያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ፕሬዚደንት፤ ለሰኔ 29 / ጁላይ 6 በሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ለመላ የማኅበረስብ አባላት ስለቀረበው የጠቅላላ ጉባኤ ጥሪና የመነጋገሪያ ዋነኛ አጀንዳዎች ያስረዳሉ።
የኢራን ፕሬዚደንት ኢራን ለዓለም አቀፍ የአቶሚክ ኃይል ኤጄንሲ ትብብሯን እንድትነፍግ የሚፈቅድ ሕግ አፀደቁ
የአውስትራሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፔኒ ዎንግ የአራትዮሹ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ፍሬያማ ነበር አሉ
የሕወሓትን ክፍፍል ተከትሎ ለሁለት የተከፈሉት የትግራይ ክልል ታጣቂዎች ወደ እርስ በእርስ ግጭት ሊያመሩ ነው የሚል ስጋት ተፈጥሯል ተባለ
ደራሲ ተሾመ ብርሃኑ ከማል፤ አዲስ ለሕትመት ባበቁት "ፕሮፌሰሮቹ" መጽሐፋቸው ስለምን ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ፕሮፌሰሮች ሙያዊ አስተዋፅዖዎች ላይ ለማተኮር እንደወደዱ ይናገራሉ።
በሥነ ጽሑፍ ሥራዎቻቸው 32 መፃሕፍትንና ከ2000 በላይ መጣጥፎችን ለአንባቢያን ያበረከቱት አንጋፋ ደራሲ ተሾመ ብርሃኑ ከማል፤ ሰሞነኛ ስለሆነው "ፕሮፌሰሮቹ" መጽሐፋቸው ተልዕኮና ይዘት ያስረዳሉ።
"በቤተ ክርስቲያንም ተከፋፍለን፣ በማኅበረሰብም ተከፋፍለን፣ በዘርም ተከፋፍለን ያሳለፍናቸው ምንም አልጠቀሙንም። አንድ ከሆንን፤ ከተባበርን፤ ከእዚህ በላይ መሥራት እንችላለን። ኅብረት የውስጥም የውጭም ጩኸቴ ነው!" አቶ ዳንኤል አለማር፤ በሜልበርን የዘፀዓት ኢትዮጵያውያን ወንጌላውያን ኅብረት አሠሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ
ኢትዮጵያን ጨምሮ 39 ሀገራት በግጭቶችና አለመረጋጋቶች ምክንያት የከፋ ረሃብና ድህነት ማዕከል እየሆኑ ስለመሆናቸው የዓለም ባንክ ባወጣው ይፋ ሪፖርት አመላከተ
ዩናይትድ ስቴትስና ኢራን በሚቀጥለው ሳምንት የቀጥታ ሁለትዮሽ ውይይት ሊጀምሩ ነው
አማኑኤል የአዕምሮ ልዩ ሆስፒታል ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ100 ሺህ በላይ ለሆኑ ተገልጋዮች የሕክምና አገልግሎት መስጠቱን ገለጠ
አቶ ዳንኤል አለማር ከዘጸአት የኢትዮጵያውያን ወንጌላውያን ህብረት የህንጻ አሰሪ ሰብሳቢ ፤ በሜልበርን ከተማ በመጪው ቅድሚ የሚመረቀው የቤተክርስቲያን ህንጻ ፤ ህብረተሰቡ ከሌለው አቅሙ ቀንሦ ለትውልዱ እና ለመጪው ትውልድ ያሳነጸው ሲሆን ፡ በህንጻ አሰሪው ኮሚቴው ስም ምስጋናዪን አቀርባለሁ ብለዋል ። አያይዘውም በምርቃቱ ላይ ሁሉም ኢትዮጵያውያን እንዲገኙ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል ።
የፈረንሳዩ ፕሬዚደንት ኢማኑኤል ማክሮን "ኢራን ውስጥ የሥርዓት ለውጥ ማድረግ ካስፈለገ በኢራን ሕዝብ እንጂ በቦምብ አይደለም" ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስን የሥርዓት ለውጥ ዕሳቤ ተቹ
በሳዑዲ ዓረቢያ ከአደንዛዥ ዕፅ ጋር በተያያዘ 37 ኢትዮጵያውያን የሞት ቅጣት ይጠብቃቸዋል
በሺህዎች የሚቆጠሩ አውስትራሊያውያን ኢራንና እሥራኤልን ለቅቀው ወደ አውስትራሊያ ለመመለስ ተመዝግበዋል
አውስትራሊያ በሩስያ ላይ ተጨማሪ ማዕቀቦችን ጣለች
በወንጀል የተገኘ ንብረትን ሕጋዊ በማስመሰልና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀሎችን የሚመረምሩ አካላት አስገዳጅ ሆኖ ሲገኝ ከግድያ በስተቀር ያሉ የምርመራ መንገዶችን የሚፈቅደውና አነጋጋሪ የሆነው አዋጅ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀደቀ
Learn how to congratulate someone on their work or wedding anniversary. - Learn how to congratulate someone on their work or wedding anniversary.
ኢትዮጵያ የባሕር በር ለማግኘት የምታደርገውን ጥረት አሜሪካ እንደምትደግፍ በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር አስታወቁ
Learn how to ask for medical help when in an emergency department. - Learn how to ask for medical help when in an emergency department.
ኳንታስ የጄት ስታር እስያ በረራውን ገታ፤ የሲድኒ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ተጠናቀቀ
ፕሪሚየር ጀርሚ ሮክሊፍ ክፍለ ሀገራዊ ምርጫ እንዲካሔድ የታዝማኒያን እንደራሴ ጠየቁ
ደራሲ ታክሎ ተሾመ፤ የSBS 50ኛ ዓመት ክብረ በዓልን አስመልክተው የSBS አስተዋፅዖዎችንና ሚና በምልሰት አንስተው ግለ አተያያቸውን ያጋራሉ።
በኢትዮጵያ ከሚገኙ 31 ባንኮች ውስጥ ሶስቱ ብቻ ሴት የቦርድ ሊቀመንበር እንዳላቸው ተመለከተ
የቀድሞው የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትርና የፑንትላንድ ፕሬዚደንት ፕሮፌሰር አብዲወሊ መሐመድ ዓሊ፤ በሶማሊያ ውስጣዊ ችግሮች፣ በሶማሊያ የኢትዮጵያ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነትና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች ዙሪያ የተካሔደ ውይይት (March 2017)። የSBSን 50ኛ ዓመት ክብረ በዓል ምክንያት በማድረግ የቀረበ።
ሼህ አብዱራህማን ሀጂ ከቢር በአውስትራሊይ የእስልምና እምነት ተከታዮች መሪ ፤ የኢድ አል አድሀ በአል ሀይማኖታዊ ዳራው ፤ ነብዩ ኢብራሂም ልጃቸው እስማኤልን ለመስእዋት ያቀረቡበት እና ፤ የአላህን ቃል መስማታቸውን እና መታዘዛቸውን ያስመሰከሩበት እንደሆነ ይናገራሉ ።
ምልሰታዊ ምልከታ፤ የSBS 50ኛ ዓመት ክብረ በዓል ጋር በተያያዘ ከድምፃዊ ፋንታሁን ሸዋንቆጨው ጋር የተካሔደ ቃለ ምልልስ።
ምልሰታዊ ምልከታ፤ የSBS 50ኛ ዓመት ክብረ በዓል ጋር በተያያዘ ከድምፃዊት ኤደን ገብረሥላሴ ጋር ያካሔድነው ቃለ ምልልስ።
አምባሳደር አንዋር ሙክታር መሐመድ በአውስትራሊያ የኢፌዴሪ ኤምባሲ ምክትል የሚሲዮን መሪ፤ የSBSን 50ኛ ዓመት ክብረ በዓል ምክንያት በማድረግ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን ያስተላልፋሉ።
አቶ ተካ አዲስ፤ የቪክቶሪያ ኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ፤ በሥራ አስፈፃሚ አባላት መካከል ተከስቶ ያለውን የአተያይ ልዩነት ማጥበብ እንዳልተቻለና መፍትሔ እንደሚያሻ ይናገራሉ። ግለ ምክረ ሃሳባቸውንም ያጋራሉ።
የሜልበርን መካነ ሰላም ቅዱስ ልደታ ለማርያም ወገብርኤል ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ፣ የሰበካ ጉባኤ አባላትና ምዕመናን የቤተክርስቲያን ግንባታ ሂደት፣ የምዕመናን ሕብረትና የአስተዋፅዖ ፋይዳዎች አንስተው ይናገራሉ።
የSBS አማርኛ አገልግሎት ራዲዮ ጋዜጠኛ ኤልያስ ጉዲሳ፤ የSBS 50ኛ ዓመት ክብረ በዓል ጋር በተያያዘ ከጋዜጠኛነት ሙያ ጅማሮው ተነስቶ የSBS ግማሽ ክፍለ ዘመን ጉዞን ከአማርኛ አገልግሎቱ ጋር አሰናስሎ ማኅበረሰባዊና ሉላዊ አስተዋፅዖዎችን ያነሳል።
ጋዜጠኛ ደመቀ ከበደ በኢትዮጵያ የSBS አማርኛ አገልግሎት ዋና ዘጋቢ ነው። የSBSን 50ኛ ዓመት ክብረ በዓል አስመልክቶ የግል የሙያ ተሞክሮዎቹን፣ የSBS እና የSBS አማርኛ አስተዋፅዖዎችን ነቅሶ ግለ አተያዩን ያጋራል።
አውስትራሊያ ውስጥ የተከሰቱ የተፈጥሮ አደጋዎች ምጣኔ ሃብት ላይ የ2 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር ወጪን ማስከተላቸው ተመለከተ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 7.7 ቢሊየን ብር ተዘርፏል ቢባልም 'የዝርፊያ ሙከራ እንጂ ዘረፋ አልተካሔደብኝም' አለ
Australia has a dark chapter of history that many are still learning about. Following European settlement, Aboriginal and Torres Strait Islander children were removed from their families and forced into non-Indigenous society. The trauma and abuse they experienced left deep scars, and the pain still echoes through the generations. But communities are creating positive change. Today these people are recognised as survivors of the Stolen Generations. - አውስትራሊያ አሁንም ድረስ አያሌዎች እየተማሩት ያለ የጨለማ ታሪክ ምዕራፍ አላት። የአውሮፓውያን ሠፈራን ተከትሎ፤ የአቦርጂናልና ቶረስ መሽመጥ ደሴት ሕፃናት ከወላጆቻቸው በኃይል ተነጥቀው ነባር ዜጎች ወደ አልሆነው ሕብረተሰብ ተወሰዱ። በውስጡ ያለፉበት የስሜት ሁከትና ጉስቁልና ጠባሳዎችን ጥሎባቸው አለፈ፤ ሕመሙ ከትውልድ ትውልድ ተሸጋግሮ እስካሁንም አለ። ይሁንና ማኅበረሰባቱ አዎንታዊ ለውጥን እየፈጠሩ ነው። ዛሬ እኒህ ሰዎች በተሰረቀው ትውልድ ተቋቋሚነት ይነሳሉ።
SBS ከ1975 አንስቶ የአውስትራሊያ መድብለባሕል የማዕዘን ደንጊያና ድምፅ ማጉሊያ ሆኖ እስከ 2025 የተጓዘበትን የግማሽ ክፍለ ዘመን ጉዞውን ጁን 9 / ሰኔ 2 ያከብራል። ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው፤ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ፕሬዚደንት ምልሰታዊ ምልከታቸውን ያጋራሉ።
የአቶ ብዙአየነህ ኃይለማርያም ይፍጠር ድንገተኛ ሕልፈተ ሕይወት ከቤተሰብ እስከ ማኅበረሰብ አባላት ብርቱ ሐዘንን ፈጥሯል። ሕልፈታቸውንም ተከትሎ አብሮ አደጋቸው አቶ ኬኔዲ ገብረየሱስ "ብዙአየነህ በማኅበረሰቡ ውስጥ ጥሩ ስም ነበረው። ሕልፈቱ በጣም የሚያስደነግጥ፤ በጣም የሚያሳዝን ነው፤ ማኅበረሰቡ ይጎዳል" ሲሉ፤ የረጅም ጊዜ ወዳጃቸው አቶ ልዑል ፍስሃ "ብዙአየነህ ላመነበት ነገር በትጋት የሚሠራ፤ ለዕውቀት ከፍተኛ ቦታ የሚሰጥ፤ ትልቅ ሰው ነበር። ሐዘናችን ጥልቅ ነው" ብለዋል። የአቶ ብዙአየነህ ፀሎተ ፍትሐት ሐሙስ ግንቦት 21 ቀን 2017 / ሜይ 29 ቀን 2025 በሜልበርን ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ከጠዋቱ 9:00 am ከተከናወነ በኋላ የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው ይፈፀማል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 14.5 ሚሊየን መንገደኞችን አጓጓዘ፤ 5.6 ቢሊየን ዶላር ገቢ አገኘ
Alfred is an Indonesian migrant, and Clinton is an Aboriginal man from Western Australia. Their friendship changed the way Alfred understood his identity as a migrant Australian. - አልፍሬድ የኢንዶኔዥያ ፍልሰተኛ ሲሆን፤ ክሊንተን የምዕራብ አውስትራሊያ ነባር ዜጎች ሰው ነው። ወዳጅነታቸው ከአልፍሬድ አውስትራሊያዊ ፍልሰተኛ ማንነት ግንዛቤ ጋር ተያይዞ ለመለወጥ በቅቷል።